ቀልጣፋ የመንገድና ትራንስፖርት አገልግሎት በለለበት ልማትን ማሳለጥ የሚቻል ባለመሆኑ፣ የገጠር መንገድ ትራንስፖርት እና መንገድ አገልግሎትን ለማጠናከር በየደረጃችን ርብርብ ማድረግ ይኖርብናል-አቶ ኃይለማርያም ተስፋዬ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ በአዲሱ በሰው ሀብት አሰራር መመሪያዎች፣ በሙስና ወንጀሎች እና በስራ ስነምግባር ላይ ለዞኖች ፣ ከተማ አስተዳደሮች ሰው ሀብት አስተዳደር ልማት አስተባባሪዎች እና ለተቋሙ ሠራተኖች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በይርጋጨፌ ከተማ እያካሄደ ነው።
በመድረኩ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይለማርያም ተስፋዬ እንደተናገሩት፣ ቀልጣፋ የመንገድና ትራንስፖርት አገልግሎት በሌለበት ልማትን ማሳለጥ የሚቻል ባለመሆኑ፣ የገጠር መንገድ ትራንስፖርት እና መንገድ አገልግሎትን ለማጠናከር በየደረጃው ርብርብ ማድረግ ያስፈልጋል።
የሕዝቡን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መሠረት በማድረግ፣ በፌደራል እና በክልሉ አቅም በየደረጃው የሚሠሩ የመንገድ ልማቶችን መለየት እና ኢኮኖሚን መደገፍ በሚችል መልኩ መገንባት እንደሚያስፈልግም አቶ ኃይለማሪያም ተናግረዋል።
ሕብረተሰቡን በመንገድ ልማት ጉዳይ ላይ ባለቤት እንዲህኑ በማድረጉ ረገድ ክፍተት ያለ በመሆኑ በቀጣይ ትኩረት ሊሆን እንደሚገባም አመላክተዋል።
የትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ ደሕንነቱ የተጠበቀ ካልሆነ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳቱ ከፍተኛ በመሆኑ ጉዳት ለመቀነስ በጥናት በትኩረት እንዲሰራም አሳስበዋል።
ዘርፉ ሰፊ ሀብት የሚንቀሳቀስበት በመሆኑ ምስጉን ሠራተኝችን ማፍራት ላይ ቢሮው ትኩረት አድርጎ እየሠራ ነው ያሉት አቶ ኃይለማሪያም፣ የግንዛቤ ማስጨበጫው ይህንን የሚደግፍ መሆኑን ተናግረዋል።
ዘጋቢ : እስራኤል ቅጣው – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶችን የስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች ለመቅረፍ የተጀመሩ ጥረቶችን ለማጎልበት የጤና አደረጃጀቶችን ሚና ማሳደግ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ
ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመግባት ዕድል ያገኙ ተማሪዎች የበለጠ ውጤታማ ለመሆን ትምህርታቸው ላይ ብቻ ሊያተኩሩ እንደሚገባ መልዕክት ተላለፈ
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ከ10 ቢልዮን ብር በላይ በጀት ለተለያዩ የልማት ስራዎች እንዲውል በተገቢው እንደሚሠራ ገለፀ