በታክስና ኢኮኖሚ ነክ ወንጀል ጉዳዮች ላይ የቀረቡ 118 መዝገቦች ውሳኔ ማግኘታቸው ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 05/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ባለፉት 9 ወራት በታክስና ኢኮኖሚ ነክ ወንጀል ጉዳዮች ላይ የቀረቡ 118 መዝገቦች ውሳኔ በማግኘታቸው ከ5 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ማደረጉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፍትህ ቢሮ አስታወቀ።
የተመዘበሩ የመንግስትና የህዝብ ሀብትና ንብረት በማስመለስ ረገድ ህብረተሰቡ የበኩሉን አበርክቶ ማደረግ እንደሚገባ ተመላክቷል።
የኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ በማከናወን መንግስት ማህበራዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ኃላፊነቱን መወጣት እንዲችል የፍትህ ተቋም እየሰራ እንደሚገኝ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ምክትል የቢሮ ኃላፊና የወንጀልና ፍትሃ ብሄር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታመነ ታደሰ ተናገረዋል።
በክልሉ ከግብር ተገዥነት በላይ በበርካታ የውጭ ምንዛሬ በሚያስገኙ ቡናና ሰሊጥ ምርቶችን ኤክስፖርት የሚደረግበት አካባቢ በመሆኑ በርካታ የኮንትሮባንድ ንግዶች ወንጀል እንደሚፈጸምበት የተመላከተ ሲሆን፥ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን በአግባቡ በመመረመርና በመክሰስ ውጤታማ እንዲሆኑ በማደረግ ረገድ በባለፉት 9 ወራት በታክስና ኢኮኖሚ ነክ ጉዳዮች ላይ 118 መዘገቦች መቅረቡን የዘረፉ ኃላፊ ገልፀዋል።
ህገ ወጥ ወንጀል የሆኑ ንብረቶችን በማሻር በማስወሰን 5 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ መደረጉን አቶ ታመነ አስረድተዋል።
የመንግስትን የወጪ ፍላጎትን ለመሙላት መንግስት በሚያደረጉት ጥረት የወንጀል ድረጊቶችን ከመከላከል አንፃርና የህግ ተጠያቂነትን ከማምጣት አንፃር በቂ ባይባልም በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ኃላፊው አስረድተዋል።
በተለይ በታክስና ኢኮኖሚ ነክ ወንጀል ጉዳዮች ምርመራና ክስ ረገድ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በመለየት ዐቃቢያን ህግ በበላይነት በመምራት የተመዘበሩ የመንግስትና የህዝብ ሀብትና ንብረትን በማስመለስ ረገድ ህብረተሰቡ የበኩን አበርክቶ ማደረግ እንደሚገባ አቶ ታመነ ገልጸዋል።
ካነጋገርናቸው ሰዎች መካከል ወይዘሮ እቴነሽ ዘገዬ ከምዕራብ ኦሞ ዞን ማጂ አከባቢ አቶ ካሳሁን ደስታ ከቤንች ሸኮና አቶ አብርሃም ፋኦ ከዳውሮ ዞን በሰጡት አስተያየት ከዚህ ቀደም የነበራቸው የታክስና ኢኮኖሚ ነክ ጉዳዮች ወንጀልን የሚያዩበት ሂደት ላይ የተሻለ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ተናገረው ይህን ለመተግበር ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ዘጋቢ፡ አብዲሳ ዮናስ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
በካፋ ዞን ጨና ወረዳ በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) የተከናወኑ የልማት ስራዎች ላይ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጋር የልምድ ልውውጥ ተደረገ
ሳታ ቴክኖሎጂ እና ቢዝነስ ኮሌጅ በአርባ ምንጭ ካምፓስ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ እና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 132 ተማሪዎችን አስመረቀ
በዕቅድ የሚመራ የመፈፀም አቅሙ ያደገ ሲቪል ሰርቫንት ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን በደቡብ ኦሞ ዞን የሳላማጎ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት ገለፀ