ለትንሣኤ በዓል አንድ ሳምንት ሲቀር የሚከበረው የሆሳዕና በዓል “ሆሣዕናን በሆሳዕና” በሚል መንፈሳዊ መርህ በሆሳዕና መምበረ ጵጵስና ደ/ገነት ቅድስት ማርያም ቤ/ያን እየተከበረ ነው
ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 05/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ያን በየዓመቱ ለትንሣኤ በዓል አንድ ሳምንት ሲቀር የሚከበረው የሆሳዕና በዓል “ሆሣዕናን በሆሳዕና” ከተማ በሚል መንፈሳዊ መርህ በሆሳዕና መምበረ ጵጵስና ደ/ገነት ቅድስት ማርያም ቤ/ያን እየተከበረ ይገኛል።
በዓሉ ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ውርንጭላ ሆኖ ከገሊላ ናዝሬት ወደ ኢየሩሳሌም የገባበትን አብነት በማድረግ የሚከበር ስለመሆኑ አባቶችና መምህራነ ወንጌል በአስተምህሮታቸው ገልፀዋል።
በእለቱም የኢየሱስ ክርስቶስን መምጣት የተመለከቱ የዘምባባ ዝንጣፊ እንዳነጠፉ ምዕመናኑ ዘምባባ እያነጠፉና በግባራቸውም በማሰር ስርዓቱን እንደሚያከብሩት ተናግረዋል።
በዓሉ ሲከበር ምዕመናኑ በሠላም፣ በፍቅር እንዲሁም እርስ በርስ በመተሳሰብና ሁሉም ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ሠላም ዘብ በመቆም ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በዓሉ በየዓመቱ በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት የሚከበር ሲሆን በዘንድሮ ዓመትም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ መምህራነ ወንጌልና ዘማሪያን እንዲሁም፥ ምዕመናን በተገኙበት በሆሳዕና መምበረ ጵጵስና ደ/ገነት ቅድስት ማርያም ቤ/ያን በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት እየተከበረ ነው።
ዘጋቢ: አማኑኤል አጤቦ – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
የፍትህ ተቋማት ተገልጋዩን ህብረተሰብ በሚመጥን መልኩ ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ ገለፁ
በተገልጋይ እርካታና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ የፍትህ ትራንስፎርሜሽንና የፍርድ ቤቶች ጥምረት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገለጸ
የዜጎችን ህይወት በማቀራረብ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ ከሚረዱ ጉዳዮች አንዱ የበጎ ፈቃድ ሥራ መሆኑ ተጠቆመ