በጎፋ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት የፍትህ ተቋማት ትራንስፎርሜሽን ዞናዊ የንቅናቀ መድረክ በሳውላ ከተማ ተካሂዷል፡፡
የጎፋ ዞን የሕዝብ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሀብታምነሽ ግራአዝማች የንቅናቄ መድረኩን ሲከፍቱ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የፍትህ ተቋማትና ፍርድ ቤቶች ውጤታማና ቀልጣፋ አገልግሎት ለህብረተሰቡ በመሰጠት የሚነሱ ቅሬታዎችን በአግባቡ መፍታት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡
የጎፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንት አቶ ፀጋዬ ፅጌ፤ በየደረጃው የሚገኙ ፍርድ ቤቶች የፍትህ አገልግሎት ለመሰጠት የሰለጠነ የሰው ሀይል በማደራጀትና በቴክኖሎጂ የታገዙ ሰራዎች ለመሰራት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡
የፍትህ ተቋማት ለህብረተሰቡ ጥብቅና በመቆም ማገልገል እንዳለባቸው አንሰተው፤ ከስነ- ምግባር አኳያ የሚነሱ ቅሬታዎች በቀጣይ በትኩረት የሚፈታ መሆኑን የዞኑ ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደመላሽ ብላቴ ተናግረዋል፡፡
የወይይቱ ተሳታፊዎች በፍትህ ተቋማት የሚስተዋሉ የፍትህ አሰጣጥ ችግሮችን በመቅረፍ በበጀት እጥረት የሚነሱ ጥያቄዎች እና በሴቶችና ህጻናት ጉዳይ የሚሰተዋሉ የፍትህ አሰጣጥ ችግሮች እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡
የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የከተማ መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ኤርምያሰ ሁሰኔ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ስንታየሁ ሙላቱ – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/