የፌደራል እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የባስኬቶ ዞን ተወላጆች አንድነት እና ወንድማማችነት ማጠናከሪያ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል

የፌደራል እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የባስኬቶ ዞን ተወላጆች አንድነት እና ወንድማማችነት ማጠናከሪያ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ፍሬው ፍሻለው በንግግራቸው የባስኬቶ ዞን ተወላጆች በዞኑ ልማት ላይ ያላቸውን ተሳትፎ እና ድጋፍ ለማሳደግ ያለመ የመወያያ መድረክ መሆኑን አስረድተዋል።

በመድረኩ የኢፌዲሪ የብዝሃ ሀብት ጥበቃ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር ፈለቀ ወልደዬስ፤ መድረኩ ከዚህ ቀደም የዞኑን ልማታዊ ተጠቃሚነትና ፖለቲካዊ ተሳትፎ በማሳደግ በሀገራዊ ግንባታ ላይ አይነተኛ ሚና ለመጫወት የሚረዳ ነው ብለዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዱፄ ታምሩ በበኩላቸው፤ የዞኑን አጠቃላይ የህብረተሰብ ክፍል በጋራ አስተሳስሮ በጋራ ራዕይ ላይ መግባባትን ለመፍጠር የተዘጋጀ ታሪካዊ ጉባኤ መሆኑን ጠቁመዋል።

አስተዳዳሪው ኢንጂነር ፍሬው ለዚሁ መድረክ የተዘጋጀውን የመወያያ ሰነድ እያቀረቡ የገኛሉ።

በመድረኩ በፌደራልና በክልል በተለያየ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ እያገለገሉ የሚገኙ የባስኬቶ ዞን ተወላጆች፣ የዞኑ ካቢኔ አባላት፣ የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር አስተባባሪ ኮሚቴ አካላት፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች እንዲሁም የሴቶችና የወጣት ተወካዮች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ: አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን