የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ምክንያት ከኢፌዴሪ “ከሰም ስኳር ፋብሪካ” ለተፈናቀሉ ተፈናቃዮች ከ5 መቶ 50 ሺ ብር በላይ በሚገመት የገንዘብ ወጪ የእህልና ዘይት ድጋፍ አደረገ

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ምክንያት ከኢፌዴሪ “ከሰም ስኳር ፋብሪካ” ለተፈናቀሉ ተፈናቃዮች ከ5 መቶ 50 ሺ ብር በላይ በሚገመት የገንዘብ ወጪ የእህልና ዘይት ድጋፍ አደረገ

ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን ዘርፈ ብዙ የህብረተሰቡን ችግር ፈቺ ተግባራት እያከናወነ እንደሚገኝ ተመላክቷል።

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳዊት ሃዬሶ በድጋፍ አሰጣጡ ወቅት እንደገለፁት፤ ዩኒቨርሲቲው በተፈጥሮ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ምክንያት ከኢፌዴሪ “ከሰም የስኳር ፋብሪካ” ለተፈናቀሉ 39 ተፈናቃይ አባወራዎች በ5 መቶ 50 ሺ የገንዘብ ወጪ ለእያንዳንዳቸው የ100 ኪሎ ግራም የጤፍና የ5 ሊትር ዘይት ድጋፍ ተደርጓል።

ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ድጋፍ በተጨማሪ በዩኒቨርሲቲው ክፍት ቦታዎች እንደ ትምህርት ዝግጅታቸው ተቀብሎ ለማስተናገድ ከዩኒቨርሲቲው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እየሰራ እንደሚገኝም ዶክተር ዳዊት ጠቁመዋል።

ዶክተር ዳዊት አክለውም በተለያዩ ምክንያቶች ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች ሁሉም የሚችለውን ድጋፍ በማድረግ ሰብዓዊ ግዴታውን ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የዩኒቨርሲቲው አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝደንት ዶክተር ኤርሚያስ ሞሊቶ በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን ዘርፈ ብዙ የህብረተሰቡን ችግር ፈቺ ተግባራት እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመው በዚህ ዕለት የተደረገ ድጋፍም የዚሁ አካል መሆኑን አመላክተዋል።

በዩኒቨርሲቲው ድጋፍ የተደረገላቸው የህብረተረብ ክፍሎችም በተደረገላቸው ድጋፍ ደስተኞች መሆናቸውን ጠቁመው ከደረሰባቸው ችግር በዘላቂነት ማገገም እንዲችሉ ሌሎችም አካላት ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጠይቀዋል።

ዘጋቢ: አማኑኤል አጤቦ – ከሆሳዕና ጣቢያችን