በምግብ እራስን ለመቻል የተያዘውን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ተባለ
“የመጋቢታዊያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች ትናንት፣ ዛሬ እና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና ”በሚል መሪ ቃል በኮሬ ዞን የፐብልክ ሰርቫንት ብልጽግና ፓርቲ ውይይት ተካህዷል።
የብልጽግና ፓርቲ ከተመሠረተበት ጊዜው ጀምሮ በኢኮኖሚያዊ፣ በፓለቲካዊና በማህበራዊ ጉዳዮች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑት ተግባራት ዙሪያ ነው ከኮሬ ዞን ፐብሊክ ሰርቫንት ብልፅግና ፓርቲ አባላት ጋር ውይይት የተደረገው፡፡
በመድረኩም የኮሬ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ብርቅነህ ጌታሁን የብልጽግና ፓርቲ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር ሁለንተናዊ ብልጽግናን ያረጋገጠበት የለውጥ ፍሬ የተበሰረበት መጋቢት ወር ነው ብለዋል።
መጋቢት ወር በኢትዮጵያ በርካታ ታሪካዊ ኩኔቶች የተከናወኑበት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን የመጡትበት እና ኢትዮጵያ ወደ ዕድገት ጉዞዋን የጀመረችበት ወር እንደሆነ የተናገሩት ኃላፊው እነዚህ ኩኔቶች መጋቢታዊያን ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች መሆናቸውን ኃላፊው አንስተዋል።
የብልጽግና ፓርቲ በሀገራችን አዎንታዊና ዘላቂ ሠላም ዕዉን ለማድረግ ዋጋ እየከፈለ የሚገኝ የለውጥ ትውልድ ያፈራንበትና ሀገራችን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በማሳደግ በምግብ እራስን ለመቻል የተያዘውን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ብለዋል አቶ ብርቅነህ ፡፡
በዞኑ “በመጋቢታዊያን ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች” በሚል መሪ ቃል በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊ እና በአስተዳደራዊ ዘርፎች እየተካሄዱ ባሉ ሦስቱም መድረኮች ላይ መነሻ የብልጽግና ፓርቲ ዕቅዶች ቀርበው በፐብሊክ ሰርቫንት የፓርቲ አባላት ውይይት ተደርጎበታል ።
በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝም እና በሌማት ትሩፋቶች፤ በኮሪደር ልማት ሥራዎችና ሌሎችም ዘርፎች ላይ ተጨባጭ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን በውይይቱ የተሳተፉ የፓርቲው አባላት የሆኑ ፐብሊክ ሰርቫንቱ ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ ብልጽግና ፓርቲ የያዛውን ዕቅድ ለማሳካት በቁርጠኝነት እንደሚንቀሳቀሱ አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ ተሾመ ፀጋዬ -ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
በሀገሪቷ ባለፉት 7 የለዉጥ አመታት የተገኙ ድሎችን በማስቀጠል የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞሳ ኢዶሳ ገለፁ
ድልና ውጤት የሚመጣው በምኞት ሳይሆን ጠንክሮ በጋራ መሥራት ሲቻል ነው ሲሉ ዶ/ር መሪሁን ፍቅሩ ተናገሩ
መጋቢት 24 በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ የፖለቲካ እጥፋት የተደረገበት ነው – ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ