ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገበታ ለሀገር አካል የሆነውን ሃላላ ኬላ ሪዞርት መርቀው ከፍተዋል፡፡
ሪዞርቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተጨማሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ የክልል ርዕሳነ-መስተዳድሮችና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተመርቋል፡፡
ሪዞርቱ የገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት አካል ሲሆን÷ ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በጥራት ተገንብቶ ተጠናቋል፡፡
የፕሮጀክቱ ግንባታም የአካባቢው ማኅበረሰብ ነባር የኪነ-ህንፃ ጥበብን ከዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂ ጋር በማናበብ ማራኪ በሆነ አግባብ ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል ነው የተባለው፡፡
ሪዞርቱ በተገነባበት ሥፍራ የሚገኘው የጊቤ ሦስት ኃይል ማመንጫ ሰው ሰራሽ ኃይቅም የሪዞርቱ ተጨማሪ ውበት መሆኑን ተጠቅሷል፡፡
በውስጡም ፕሬዚዳንታዊ የእንግዳ ማረፊያዎች፣ ዘመናዊ መኝታ ክፍሎችና ሌሎች የመዝናኛ ሥፍራዎችን የያዘ ነው፡፡
የሪዞርቱ መገንባትም ለአካባቢው ማኅበረሰብ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ነው የተጠቆመው፡፡
More Stories
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሪጅን በሚዛን ዲስትሪክት አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ
የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በዘላቂነት ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የህግ ትምህርት ቤቶች መካከል የተካሄደው 9ኛው የምስለ ችሎት ውድድር በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አሸናፊነት ተጠናቀቀ