1ሺህ 446ኛ የኢድ አልፈጥር በዓል ስናከብር ሠላማችንን በማፅናት ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ: መጋቢት 21/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) 1ሺህ 446ኛ የኢድ አልፈጥር በዓል ስናከብር የተጀመረውን የሠላም ጥረት በማፅናት ሊሆን እንደሚገባ የማረቆ ልዩ ወረዳ አስተዳደር አስታውቋል።
1446ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በማረቆ ልዩ ወረዳ ቆሼ ከተማ በሐይማኖታዊ ስነ ስርዓት በድምቀት ተከብሯል።
የማረቆ ልዩ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጀማል አማሮ በዚህ ወቅት እንዳሉት፥ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ፆሙን በሶላት፣ በዱኣ እና ለአገራችን ሠላም የበኩሉን አስተዋዕፆ በማድረግ በብዙ ኩነቶች ያሳለፈበት እንደነበር ጠቁመው፥ ዛሬ የበዓሉ ማጠቃለያ በደማቅ ሐይማኖታዊ የተክቢራ ስነ ስርዓት ተካሂዷል ብለዋል።
በዚህ ወር ካከናወናቸው ነገሮች መካከል አንዱ የሠላም ግንባታ ስራችንን በማጽናት በቀጠናችን ላይ የቆየውን የግጭት ሁኔታ በዘላቂነት ለመፍታት መንግስት በጀመረው አግባብ ህዝቡን ደግፎ ሰላሙ እንዲፀና ለማድረግ ጥረት መደረጉን ጠቁመው፥ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከፈጣሪው ጋር የሚገናኝበት ቅዱስ ወር ረመዳን በመሆኑ፥ህዝቡ ሰላሙን በማፅናት ረገድ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ አመላክተዋል።
አቶ ከድር መስቀሎ የቢላል መስኪድ ሰብሳቢ በበኩላቸው፥ ረመዳን ፆም ከአሏህ ጋር የምንገናኝበትና የዕዝነት ወር በመሆኑ፥ ምስኪኖችን የምንረዳበት፣ በአንድነት፣ በሠላምና በፍቅር የምናሳልፍበት በዓል ነው ብለዋል።
በማረቆ ልዩ ወረዳ እስልምና ጉዳዮች ሰብሳቢ አቶ ሱሌማን ሰብሮ፥ በዓሉን በመቻቻል፣ ዕርስ በዕርስ በመረዳዳትና ችግረኛ ወገኖቻችንን በማገዝ የዕስልምና አስተምህሮ በሚያዘው መሰረት ሊሆን እንደሚገባ ገልፀው፥ በአጎራባች አከባቢ ከምስራቅ ጉራጌ ዞንና ማረቆ ልዩ ወረዳ የጋራ ኢፍጣር ስነ ስርዓት በማድረግ፥ ፆሙ የሰላም፣ የፍቅር፣ የይቅርታና የአብሮነት መሆኑን በሚያሳይ መልኩ መከናወኑን አስረድተዋል።
በመላው ዓለም በሚገኙ ሙስሊሞች ዘንድ የሚከበረው 1ሺህ 446ኛ የኢድ አልፈጥር በዓል በማረቆ ልዩ ወረዳ ቆሼ ከተማ በድምቀት ሲከበር፥ የልዩ ወረዳው አመራር አካላትና የዕምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በሶላት ስነ ስርዓት አክብረዋል።
ዘጋቢ: ዘላለም ተስፋዬ
More Stories
“ብልፅግና እና ሰው ተኮር ስራዎች በሚል መሪ ቃል “በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሃድያ ዞን በሆሳዕና ከተማ ከፍተኛ አመራሮች የተለያዩ የመጋቢት ወር የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል
የለውጡ መንግስት ያስመዘገባቸውን ድሎችን በላቀ ሀላፊነትና ቁርጠኝነት ልናስቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ምክንያት ከኢፌዴሪ “ከሰም ስኳር ፋብሪካ” ለተፈናቀሉ ተፈናቃዮች ከ5 መቶ 50 ሺ ብር በላይ በሚገመት የገንዘብ ወጪ የእህልና ዘይት ድጋፍ አደረገ