የጌዴኦ ዞን አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) በዲላ ሁለገብ ስታድየም ተገኝተው ለ1ሺህ 4 መቶ 46ኛው ዒድ አል ፈጥር በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አሰተላለፉ

የጌዴኦ ዞን አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) በዲላ ሁለገብ ስታድየም ተገኝተው ለ1ሺህ 4 መቶ 46ኛው ዒድ አል ፈጥር በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አሰተላለፉ

ሀዋሳ፡ መጋቢት 21/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በዲላ ሁለገብ ስታድየም በዓሉ ሲከበር የተገኙት የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) ለ1 ሺህ 4 መቶ 46ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዓሉን በታላቁ የረመዳን ወቅት ልዩነቶቻችን ሳይገድቡን፣ የኢፍጣር ማዕድ በአብሮነት እንደተቋደስን ሁሉ ለሀገራችን ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና ወንድማማችነትን ማጠናከር ይኖርብናል ብለዋል፡፡

የእስልምና እምነት ተከታዮች በረመዳን ፆም ወቅት ያሳዩት የፍቅር፣ የመተሳሰብ፣ የመደጋገፍ እና የአብሮነት እሴቶች ለሀገር ግንባታም የጎላ ፋይዳ እንዳለው የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶክተር መስፍን ደምሴ ገልጸዋል።

የዲላ ከተማን ምቹና ሳቢ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የሙስልሙ ማህበረሰብ በልማት ሥራዎች ላይ በመሳተፍ የራሳቸውን አሻራ እንዲያሳርፉ ጥሪ አቅርበዋል።

ለመላው ሙስልም ማህበረሰብ የዒድ አል ፈጥር በዓል የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ እና አንድነት እንዲሆንላቸው አስተዳደሪዎቹ መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

በበዓሉ ስነ-ስርዓት ላይ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር)፣ የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አበባየሁ ኢሳይያስ፣ የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መስፍን ደምሴ (ዶ/ር) ጨምሮ የክልል፣ የዞንና የዲላ ከተማ አመራሮች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፡ ተስፋዬ ጎበና – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን