የዒድ አል-ፈጥር በዓል በሀላባ ዞን እየተከበረ ነው

የዒድ አል-ፈጥር በዓል በሀላባ ዞን እየተከበረ ነው

1446ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል በሀላባ ዞን ቁሊቶ ከተማ በሚገኘው የኢድ አደባባይ የእስልምና እምነት ተከታዮች በተገኙበት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በረመዳን ወር የታየውን አብሮነትና መተሳሰብ በማስቀጠል እና ለተቸገሩ በማገዝ ይህን የዒድ አል-ፈጥር በዓል ማክበር እንደሚገባም ተገልጿል።

በበዓሉም በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መሀመድ ኑሪዬን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ የእምነቱ ተከታዮች በዓሉን እያከበሩ ይገኛሉ።

በዚህም የዒድ ሶላት ሥነ-ሥርዓት እና ሌሎች ሀይማኖታዊ ተግባራት በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።

ዘጋቢ፡ ቃለአብ ፀጋዬ