የ1 ሺህ 4 መቶ 46ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በጌዴኦ ዞን ዲላ ሁለገብ ስታዲየም በድምቀት እየተከበረ ነው
የጌዴኦ ዞን እስልምና እምነት አባቶችም ለዒድ አል ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማስተላለፍ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
1 ሺህ 4መቶ 46ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓልን የእምነቱ ተከታዮች በሶላት፣ ቴክብራ በስግደትና በተለያዩ ኃይማኖታዊ ክዋኔዎች በዲላ ከተማ ሁለገብ ስታዲየም በድምቀት በማክበር ለይ ናቸው።
ከእስልምና እምነት አባቶች የተለያዩ ኃይማኖታዊ መልዕክቶች ስለ ኢድ አል ፈጥር በዓል እያስተላላፉ ነው።
የኢድ አል-ፈጥር በዓል በመላው ዓለም በሚገኙ ሙስሊሞች ከሚከበሩት በዓላት አንዱ ሲሆን የተከበረው የረመዳን ወር የፆም፣ የፀሎት እና የዕዝነት እንዲሁም የአላህን ምህረት እየተማጸኑ ያሳለፉበት ወር መሆኑ ይታወሳል።
ህዝበ ሙስልሙ በዓሉን ሲያከበር የተቸገሩትን፣ አቅመ ደካሞችን እና ጎረቤቶቻቸውን በማሰብ መሆን እንደለበት ተገልጿል።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ፣ የአንድነትና የአብሮነት እንዲሆንላቸው የኃይማኖት አባቶቹ መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፡ ተስፋዬ ጎበና – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
በሀገሪቷ ባለፉት 7 የለዉጥ አመታት የተገኙ ድሎችን በማስቀጠል የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞሳ ኢዶሳ ገለፁ
ድልና ውጤት የሚመጣው በምኞት ሳይሆን ጠንክሮ በጋራ መሥራት ሲቻል ነው ሲሉ ዶ/ር መሪሁን ፍቅሩ ተናገሩ
መጋቢት 24 በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ የፖለቲካ እጥፋት የተደረገበት ነው – ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ