በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለዜጎች ዘላቂ የስራ ዕድል ለመፍጠር እየተደረገ ያለው ጥረት ውጤታማ መሆኑ ተገለፀ

ከስራ አጥነት ተነስተው ስራ እድል ፈጠራን ቢዝነስ በማድረግ ተጠቃሚ መሆናቸውን የክልሉ ወጣቶች ተናግረዋል።

ስራ አጥ ዜጎች የስራ እድል ተጠቃሚና በስራቸው ውጤታማ እንዲሆኑ በሚደረገው ሁሉ አቀፍ እንቅስቃሴ ውስጥ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በሁሉም ዘርፎች ያሉ እድሎችን አሟጦ በመጠቀም የክልሉ ዜጎች የስራ ዕድል ተጠቃሚ መሆን ችለዋል።

እነዚህ በክልሉ በተለያዩ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ላይ የተደራጁ ወጣቶች በተሰማሩበት ዘርፍ ከራሳቸው ባለፈ ለሀገር ኢኮኖሚ አበርክቷቸው ከፍ ያለ እንደሆነና መንግስት እንደ ሀገር ትርጉም ባለው ደረጃ የስራ አጥነትን ችግር ለመቀነስ እያደረገ ያለው ጥረት ይበል የሚያሰኝና ሊጠናከር የሚገባ ስለመሆኑም የክልሉ ወጣቶች ገልፀዋል።

ክልሉ በሁሉም ዘርፎች ያሉ እድሎችን በመጠቀም ዜጎች የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረጉ ተግባር በተጠናከረ መልኩ እየተሰራበት ሲሆን ለ350 ሺህ ስራ አጥ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን የገለፁት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ መሐመድ ኑሪዬ(ዶ/ር) ናቸው።

ዘጋቢ፡ ቴዎድሮስ ወርቅነህ