በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኮሬ እና ቡርጂ ዞኖች አዋሳኝ አካባቢዎች ወቅታዊ የፀጥታ ጉዳዮችና በዘላቂ ሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው
በምክክር መድረኩ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወገኔ ብዙነህ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ጎአ፣ የ37ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ካሳዬ ተገኝ፣ የኮሬ ዞን፣ የምዕራብ ጉጂ ዞንና የቡርጂ ዞን አስተባባሪዎችና የፀጥታ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
መድረኩ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጠናከር ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስተጋብሮችን በማስፈን በአካባቢው ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ እንደሆነም ተገልጿል።
ዘጋቢ፡ ተሾመ ፀጋዬ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
ለአፍሪካ ተምሳሌት ከሆነ ምርጫ ወደ መንግሥት ምስረታ!
ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ህዝብ፤ ታላቅ ርዕይ
የጉራጌ ሕዝብ ራስ አገዝ ልማት ድርጅት ለአካል ጉዳተኛ ሕፃናት የትምህርት ቁሳቁስ በመደገፍና ግንዛቤ በመፍጠር የመማር መብታቸው እንዲጠበቅ እየሠራ እንደሚገኝ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ገለፀ