ሀዋሳ፡ መጋቢት 17/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የዱራሜ ክላስተር “ትላንት ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና የመጋቢታዊያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች” በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ የተካሄደ ነው።
በውይይት መድረኩም በዱራሜ ክላስተር የሚገኙ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ደንና አካባቢ ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሃም መጫ፤ ባለፉት የለውጥ አመታት በተለያዩ ዘርፎች በርካታ ተግባራት መተግበራቸውን አንስተው ይህ መድረክም እነዚህ ለውጦች የሚነሱበትና የቤት ስራ በሚጠይቁ ተግባራት ላይም በቁጭት ለመስራት እንዲያስችል የተዘጋጀ ነው ብለዋል።
ብልፅግና ፓርቲ ሀገርን ወደ ሁለንተናዊ እድገት ለማሻገር እንዲሁም ሁሉም በእኩልነት የሚሳተፍበትን ስርአት ከመዘርጋት ጀምሮ የሚታዩ ውጤቶችን ማስመዝገቡን የተናገሩት ኃላፊው፤ በዚህም የጥላቻ ግንብን በማፍረስና ብሄራዊ ትርክትን በመገንባት ሀገር የገጠማትን ፈተና በድል እድትሻገር የሚያስችሉ ስራዎችም በትኩረት ስለመተግበራቸው አንስተዋል።
ዘላቂ ሰላምን ማስፈን፣ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት መሻገር እንዲሁም ዲፕሎማሲ ስራዎችን ማጠናከርና ሀገር በአለም አቀፍ መድረኮች ተሰሚነቷ እንዲጨምር ማድረግ በለውጡ አመታት በትኩረት የተተገበሩ ስራዎች መሆናቸውንም ኃላፊው ተናግረዋል።
እንደ ሀገር ብሎም እንደ ክልል የተጀመሩ ውጤታማ ተግባራትን ለማስቀጠልና አሁንም ህዝብን የሚፈትኑ ተግባራትን ለማስተካከል ሁሉም በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባውም ኃላፊው በመልእክታቸው አሳስበዋል።
በውይይት መድረኩ በለውጡ አመታት የተከናወኑ ተግባራትና ቀጣይ የቤት ስራዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።
ዘጋቢ፡ ቃለአብ ፀጋዬ

More Stories
የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶችን የስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች ለመቅረፍ የተጀመሩ ጥረቶችን ለማጎልበት የጤና አደረጃጀቶችን ሚና ማሳደግ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ
ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመግባት ዕድል ያገኙ ተማሪዎች የበለጠ ውጤታማ ለመሆን ትምህርታቸው ላይ ብቻ ሊያተኩሩ እንደሚገባ መልዕክት ተላለፈ
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ከ10 ቢልዮን ብር በላይ በጀት ለተለያዩ የልማት ስራዎች እንዲውል በተገቢው እንደሚሠራ ገለፀ