ሀዋሳ: መጋቢት 17/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በከተሞች የሚከናወኑ የኢኒሼቲቭ ስራዎች በተያዘላቸው የጊዜ ማዕቀፍ ውስጥ ሊሆን እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስራክሽን ቢሮ አስታወቀ።
በከተሞች እየተከናወኑ የሚገኙ የኢኒሸቲቭ ስራዎች የደረሱበትን የአፈጻጸም ደረጃ የሚገመግም መድረክ በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኢንዱስትሪ ክላስተር አስተባባሪና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤል በዚህ ወቅት እንደገለጹት፥ በክልሉ የሚከናወኑ የኮሪደር ልማት፣ የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት፣ የአገልግሎት ማዘመን፣ የኢንዱስትሪ ቦታዎች ማካለልና የፅዳት፣ ውበትና አረጓዴ ልማት ስራዎች፣ የደረሱበት አፈፃፀም ደረጃ ከዞንና ከከተማ አሰተዳደር አመራሮች ጋር መገምገምና የጋራ መግባባት መያዝ እንደሚገባ አመላክተዋል።
ስታንዳርዶችን በሚያስጠብቅ ደረጃ መስራት ይጠይቃል ያሉት ኃላፊው፥ በከተሞች የሚከናወኑ የልማት ተግባራትን ማዘመንና ወደ ስታንዳርድ ማምጣት ወደ ስማርት ሲቲ ለሚደረገው ጉዞ መሠረት በመጣል የሚያጋጥሙ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የማዘመን ስራዎች ላይ ያተኮረ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በክልሉ ከተሞች የሚከናወኑ የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክቶች የተለዩና ወደ ስራ የገቡ አፈፃፀሞች የደረሱበትን ደረጃ ማወቅ ተገቢ መሆኑን ጠቁመው፥ የሚገነቡ ፕሮጀክቶች ሂደት የፊዚካልና የፋይናንሽያል አፈጻጸም ያሉበትን ሁኔታ መወያየት እንደሚገባ አስረድተዋል።
የኢንዱስትሪ ዞን ማካለል ስራ በጋይድ ማፕ የታገዘና የተከለለ መሬት በሄክታር ተለይቶ መረጋገጥ አለበት ያሉት አቶ ስንታየሁ፥ ለዚሁ አላማ ተብለው የተለዩ ቦታዎችን በተለይ ኢንዱስሪዎችን በክላስተር ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
በከተሞች ያለው የአረንጓዴ ልማት ስራ የአመለካከት፣ እውቀትና የምንመራበት መንገድ በትኩረት መፈተሽ እንደሚያስፈልግ አመላክተው፥ ከተሞች የአረንጓዴ ልማት ተግባራት ሽፋን ግብ ሊኖራቸው እንደሚገባ ተጠቁሟል።
ህብረተሰቡን ያሳተፈ ፅዱ፣ ውብና ለነዋሪዎች ምቹ የሆነ ስራ መስራትና ነዋሪውን በየአካባቢው በማደራጀት መቀናጀትና የአከባቢ እንክብካቤና የጥበቃ ስራዎች ማጠናከር እንደሚገባ ተመላክቷል።
በክልሉ እየተከናወኑ በሚገኙ የኮሪደር ልማት፣ የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት፣ የአገልግሎት ማዘመን፣ የኢንዱስትሪ ቦታዎች ማካለልና የፅዳት፣ ውበትና አረጓዴ ልማት ስራዎች፣ የደረሱበት አፈፃፀም አስመልክቶ የዞንና ከተማ አሰተዳደር አመራሮች ያሉበትን የአፈፃፀም ደረጃ የሚያመላክት ሪፖርታቸውን እያቀረቡ ነው።
በውይይት መድረኩ ከሁሉም የክልሉ ዞኖቾ፣ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች፣ ማዘጋጃ ቤት ስራአስኪያጆችና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።
ዘጋቢ፡ ዘላለም ተስፋዬ
More Stories
የማህበረሰቡን አንድነት፣ ሠላምና ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ባህላዊ እሴቶችን ጠብቆ በማቆየት ለትውልድ እንዲተላለፉ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ
በክህሎት ፣ በቴክኖሎጂና በተግባራዊ ጥናትና ምርምር ሥራዎች ውድድር ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ አስታወቀ
በሀገሪቷ ባለፉት 7 የለዉጥ አመታት የተገኙ ድሎችን በማስቀጠል የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞሳ ኢዶሳ ገለፁ