በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን ከቃል እስከ ባሕል በሁለተኛው የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔ አቅጣጫዎች ላይ የወጣቶች ክንፍ ሚናን በተመለከተ የምክክር መድረክ በጂንካ ከተማ ተካሂዷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ወጣት አስቻለው መሸሻ፤ በክልሉ በሁሉም አካባቢ የሚደረገውን የወጣቶች ክንፍ መድረክ ዓላማን አስረድተዋል።
የአሪ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ጉራልቅ ይዥማልቅ ለወጣቶች ባስተላለፉት መልክት፤ ወጣቱ ሕብረብሔራዊነት እና ገዥ ትርክትን በማጠናከር ለአንድነትና ለሀገር ግንባታ የድርሻቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል።
አቶ ጉራልቅ አክለውም በዞኑ ያሉ ፀጋዎችንና ዕድሎችን በመጠቀም ፓርቲው የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።
የዞኑ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደለ ገበየሁ በበኩላቸው፤ ፓርቲው የወጣቱ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎችና አቅጣጫዎችን ለታዳሚው በሰነድ ያቀረቡ ሲሆን ለተግባራዊነቱ ሁሉም በጋራ ሊረባረቡ እንደሚገባ በውይይት መድረኩ የተሳተፉ ወጣቶች አንስተዋል።
በዞኑ ያሉ ሁሉንም ወጣቶች ተደራሽ ለማድረግ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ተመሳሳይ መድረኮችን በማዘጋጀት የወጣቱ እኩል ተሳታፊነትንና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንደሚሠራም በውይይቱ ማጠቃለያ ተገልጿል።
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ሳውላ ካምፓስ ለ9ኛ ጊዜ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 121 ተማሪዎችን አስመረቀ
ዲግሪው “ወረቀት ብቻ ሳይሆን፣ የሀገር ተስፋና የትውልድ ኃላፊነት ነው” – አፈወርቅ ካሱ (ፕ/ር)
በክልሉ የተጀመሩ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የድጋፍና ክትትል ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ገለጹ