ከ200 የሚበልጡ የኢትዮጵያ ከተሞች ከንቲባዎች በአዲስ አበባ የለውጡን ስኬት ማሳያ የሆኑ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን መጎብኘታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትሰሰር ገጻቸው “ከ200 በላይ ለሚሆኑ የኢትዮጵያ ከተሞች ከንቲባዎች በመዲናዋ ከለውጡ ወዲህ አቅደን በመፈፀም ያስገኘናቸውን ስኬቶችንና ውጤታችንን ያሳዩ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን እንዲሁም ሰው ተኮር ስራዎቻችንን አስጎብኝተናል” ብለዋል።
በመቀጠልም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር የበለፀጉ ከተሞችን ለመፍጠር ከንቲባዎች በሚጫወቱት ሚና ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገን ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ተቀብለናል ሲሉም ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ የከተማዋ ገጽታ ተቀይሮ የቱሪስት መዳረሽ ሆናለች ያሉት ከንቲባዋ÷ ፕሮጀክት መጀመር ብቻ ሳይሆን በጊዜ ማጠናቀቅ የሚያስችል የስራና የአሰራር ባህል ተፈጥሯል በማለት ገልጸዋል።
በመዲናይቱ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች አለሁ የሚል አሳቢ አመራር መፈጠሩንም አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ ከተሞች ከንቲባዎች ከዚህ ስኬት ልምድ ወስደው ከተሞቻቸውን የማላቅ እና የነዋሪዎችን የኑሮ ጫና የሚያቃልሉ ሰው ተኮር ስራዎች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።
More Stories
የዲላ ከተማን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማፋጠን በትኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ
በክልሉ ያሉ የገቢ አማራጮችን በተገቢው አሟጦ ከመሰብሰብ አንፃር ያሉ ውስንነቶች ማረም እንደሚገባ ተገለፀ
ቡናና ሻይ ቅመማቅመም ምርቶችን አብዝተዉ በማምረት ኢኮኖሚያቸዉን እያሳደጉ መሆናቸዉን በዳዉሮ ዞን ድሳ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ