እንደ ሀገር የተጀመረው የበጎ አገልግሎት መጠናከር እንዳለበት ተጠቆመ
ሀዋሳ፡ ጳጉሜ 03/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በጎን ማሰብ ስለተረፈን ሣይሆን ከውስጥ የሚመነጭ መልካም አስተሳሰብ ነው ሲሉ የቦንጋ መሀል ከተማ ሚሊኒየም እድር አባላት ገለጹ።
የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ካሣ ከበደ በቦንጋ ሚሊንየም እድር አዳራሽ በመገኝት የበጎ አድራጎት ቀንን ምክንያት በማድረግ ባደረጉት ንግግር እንደ ሀገር የተጀመረው የበጎ አድራጎት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
ከዚህ ቀደምም ሆነ አሁን በበጎ ተግባሩ ሞዴል የሆነው ይኼው እድር የድሀ ድሀ የሆኑ ቤተሰቦችን ለመርዳት የሚያደርገው ሥራ የሚበረታታ ነው ብለዋል።
የትኛውም በጎ አድራጎት ለራስ ስንቅ ነው ያሉት ሀላፊው እንደ ሀይማኖት አስተምሮ መሰጠት መቀበል እንደሆነና ዝቅ ብሎ ማገልገልን ሁሉም ዜጋ ተግባራዊ ሊያደርግ እንደሚገባ ገልፀዋል።
የእድሩ አባላት እየተገበሩ ያለውን ሥራ ሌሎች እድሮችም ተግባራዊ ሊያደሮጉ ይገባል ብለዋል።
የእድሩ ሰቢሳቢ አቶ አጥናፉ ወልደጻድቅ በበኩላቸው የእድሩ አባላት ሲሞቱ ከመቅበር ባለፈ በቁመና እያሉ የመርዳትና የመጠያየቅእንዲሁም አቅመ ደካሞችንና ወላጅ የሌላቸውን ህጻናት በመደገፍ የበኩላቸውን እየተወጡ መሆናቸውን አስረድተዋል።
የምንደግፈው ስለተረፈንና ስለሞላን ሳይሆን የተቸገሩትንና አቅም የሌላቸውን ግለሰቦች ካለን በማካፈል የመርዳት ባህልን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
ለአመት በዓል መዋያ ከዕድሩ አንድ ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ የተደረገላቸው ወ/ሮ አበበች ወልዴ እና ወ/ሮ ቦጋለች ተረፈ ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።
ዘጋቢ፡ ሐብታሙ ገብሬ – ከቦንጋ ጣቢያ
More Stories
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ 120 የህክምና ዶክተሮችን አስመረቀ