በስልጤ ዞን ሚቶ ወረዳ 25 አዳዲስ ቤቶች እና 17 ያረጁ ቤቶች በበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተገንብተው ለአቅመ ደካሞች እና ለመከላከያ ቤተሰቦች ተሰጡ

በስልጤ ዞን ሚቶ ወረዳ 25 አዳዲስ ቤቶች እና 17 ያረጁ ቤቶች በበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተገንብተው ለአቅመ ደካሞች እና ለመከላከያ ቤተሰቦች ተሰጡ

ሀዋሳ፡ ጳጉሜ 03/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በስልጤ ዞን ሚቶ ወረዳ 25 አዳዲስ ቤቶች እና 17 ያረጁ ቤቶች በበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተገንብተው ለአቅመ ደካሞች እና ለመከላከያ ቤተሰቦች ተሰጥተዋል፡፡

በክረምቱ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች የተሰሩ የመንገድ፣ የአካባቢ ጥበቃና የተለያዩ የልማት ሥራዎች የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰባሀድን ሎባ ገልፀዋል፡፡

አስተያየት የሰጡ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች የህብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍ ሁሉም ሰው በየአካባቢው የድርሻውን የሚወጡ ከሆነ የአገሪቱ ችግር በቀላሉ እንደሚቀረፍ ገልፀዋል፡፡

ዘጋቢ፡ አበባ ሌንዲዶ