በጎነት የህሊና እርካታ ይሰጣል – በጎ አድራጊ ወጣቶች
ሀዋሳ: ጳጉሜ 03/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በጎ ማድረግ የህሊና እርካታ የሚሰጥ በመሆኑ ሰዎች ለበጎ ሥራ ሊነሳሱ እንደሚገባ በቡታጅራ ከተማ በጎ አድራጊ ወጣቶች ተናግረዋል::
በቡታጅራ ከተማ ጳጉሜ 03 ቀን 2015 ዓ.ም የበጎነት ቀን በሚል በተለያዩ በጎ ተግባራት ተከብሮ ውሏል::
የከተማ ፅዳት ሥራ ሲያከናውኑ ያገኘናቸው የከተማዋ ወጣቶች መልካም ማድረግ እና በጎ ተግባር መፈፀም ካሳደጉን ወላጆቻችን የተማርነው ነገር ነው ብለዋል::
ይህ በጎ ሥራ በምንም ሊተካ የማይችልና የመንፈስ እርካታ የሚያስገኝ መሆኑን ገልጸዋል::
ዛሬ በመላ ኢትዮጵያ በሚከበረው የበጎነት ቀን ላይ ይህን ተግባር መፈፀም በመቻላችን ደስተኞች ነን ሲሉ ተናግረዋል::
ሌሎችም ወጣቶች መሠል ተግባራትን በማድረግ ለራሳቸውም ሆነ ለሌላ ሠው የደስታ ምንጭ መሆን እንደሚችሉ ጠቁመዋል::
የቡታጅራ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ፅህፈት ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ አማን በድሩ በበጎነት ቀን የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል ብለዋል::
የከተማ ፅዳት፣ የአልባሳት ድጋፍ፣ የደብተር ድጋፍና የእስክርቢቶ ድጋፍ እንዲሁም የአረጋዊያን ቤቶችን የማደስና ማዕድ የማጋራት ሥራ የመርሀግብሩ አካል ናቸው ብለዋል::
በተለይ ወጣቱ ለበጎ ሥራ እያሳየ ያለው ተነሳሽነት የሚደነቅ ነው ያሉት ምክትል ሃላፊው ላከናወኑት መልካም ተግባርም ምስጋና አቅርበዋል::
ዘጋቢ: ማሬ ቃጦ
More Stories
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ 120 የህክምና ዶክተሮችን አስመረቀ