የ2025 አፍሪካ ዋንጫ ውዝግብ በሴኔጋል አሸናፊነት ተቋጨ

የ2025 አፍሪካ ዋንጫ ውዝግብ በሴኔጋል አሸናፊነት ተቋጨ

ዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት (ካስ) በ2025 የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊነት ዙሪያ ተነስቶ የነበረውን ከፍተኛ ውዝግብ በመፍታት፣ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ያሳለፈውን ውሳኔ በመሻር ዋንጫው ለሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን እንዲሰጥ ወስኗል።

ውዝግቡ የተነሳው የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን ማን ይሁን በሚለው ጉዳይ ላይ ካፍ ካሳለፈው ውሳኔ ጋር በተያያዘ ነው።

ካፍ ቀደም ሲል ሴኔጋል ጨዋታው ሳይጠናቀቅ ከሜዳ ወጥታለች በሚል ምክንያት የዋንጫ አሸናፊነቱን ለሞሮኮ ሰጥቶ ነበር።

የካፍን ውሳኔ ያልተቀበለችው ሴኔጋል ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት (ካስ) በመውሰድ ይግባኝ ብላለች።

ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ በመጨረሻ የካፍን ውሳኔ በመሻር ሴኔጋልን በይግባኙ አሸናፊ አድርጓል።

በዚህም መሠረት ካፍ የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊነትን ለሞሮኮ ለመስጠት የወሰነው ውሳኔ ተሽሯል።

የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮንነት ሙሉ በሙሉ ለሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን እንዲሰጥ ተወስኗል::

በመጨረሻም በሜዳ ላይ እና በጠረጴዛ ዙሪያ ሲካሄድ የቆየው የፍትሕ ፍልሚያ በሴኔጋል አሸናፊነት በይፋ ተቋጭቷል።

የካስ ይህ ብይን በአፍሪካ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ትልቅ የሕግ እና የውድድር ምዕራፍ የከፈተ ሲሆን፣ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድንም የአህጉሩን ታላቅ ዋንጫ በሕጋዊ መንገድ በማረጋገጥ ድሏን አፅንቷል።

ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ