‎የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን መከበሩ ቱባ ባህሎችን ለማስተዋወቅ አስተዋፅኦ አለው – የኮሬ ዞን ምክር ቤት‎

‎የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን መከበሩ ቱባ ባህሎችን ለማስተዋወቅ አስተዋፅኦ አለው – የኮሬ ዞን ምክር ቤት‎

‎የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን መከበሩ ያሉን ቱባ ባህሎችን ለማስተዋወቅና አንድነትን ለማጠናከር አስተዋፅኦ እንዳለው የኮሬ ዞን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡‎

በየዓመቱ ኅዳር 29 ቀን የሚከበረው ‎የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከበር የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት የፀደቀበትም ዕለት ነው።‎

‎የኮሬ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ወ/ሮ ዝናሽ  ሃይሌ የበዓሉ መከበር ዋና አላማ የብሔር ብሔረሰቦችን ባህል፣ አንድነትንና የእርስበርስ  ትስስርን ማጠናከር እንደሆነ ገልፀዋል፡፡‎

‎ቀኑ መከበሩ የራስን ጠቃሚ ባህል ለማስተዋወቅም ሆነ አንዱ ብሔር ከሌላው ጋር እንዲተዋወቅ ከማድረግ አንፃር ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ሲሉ ተናግረዋል።‎

‎የኮሬ ብሔረሰብም ቀኑ መከበር ከጀመረ ወዲህ የራሱን ቱባ ባህሎችን ለአለም በማስተዋወቅና ከሌላው የኢትዮጵያ ብሔሮች ጋር መልካም ግንኙነት በመፍጠር ተጠቃሚ በመሆን ላይ ይገኛል ብለዋል። ‎

‎የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዞን ደረጃ  በሁሉም መዋቅሮች በጎ ተግባራትን በማድረግ፣ ታሪካዊ ቦታዎችን በመጎብኘትና በተለያዩ ኩነቶች በመከበር ላይ እንደሚገኘ ገልፀዋል።‎

በዞን ማዕከል ‎የማጠቃለያ ፕሮግራምም ለህብረተሰቡ በህገመንግስቱ ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠርና በተለያዩ አዝናኝ ዝግጅቶ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል ብለዋል።‎

‎ህብረተሰቡ ህገመንግስቱ ያጎናፀፈውን መብት በመጠቀም ቀኑን ከማክበር ባለፈ የራሱን ባህል ጠንቅቆ በማወቅና ለሌላውም በማስተዋወቅ ማክበር አለበት ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።‎

‎የዘንድሮው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል “በብዝሃነት የደመቀች በምክክር የፀናች ስልጡን ኢትዮጵያ” በምል መሪ ቃል ህዳር 29 ቀን 2019 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል አዘጋጅነት በጅማ ከተማ ይከበራል።‎

‎ዘጋቢ፡ ለምለም ኦርሳ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን