‎ወጣቶች ሚዲያ ሲጠቀሙ ከፋፋይ ከሆነ አጀንዳ በመውጣት የማህበረሰቡን አንድነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ሊያተኩሩ ሊገባል‎

‎ወጣቶች ሚዲያ ሲጠቀሙ ከፋፋይ ከሆነ አጀንዳ በመውጣት የማህበረሰቡን አንድነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ሊያተኩሩ ሊገባል‎

‎ወጣቶች ሚዲያ ሲጠቀሙ ከፋፋይ ከሆነ አጀንዳ በመውጣት የማህበረሰቡን አንድነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ሊያተኩሩ እንደሚገባ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዴኦ ዞን አስተዳደር አሳሰበ።‎

‎የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የሚዲያና የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ግምገማና የማህበራዊ ሚዲያን አጠቃቀም ለማሻሻል የሥልጠና መድረክ አካሂዷል።‎

‎ሚዲያ ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት፣ ለሰላምና የዴሞክራሲ ምህዳር ለማስፋት ያለው አበርክቶ የላቀ በመሆኑ አጠቃቀማችንም ኃላፊነትንና ተጠያቂነትን በተላበሰ መልኩ ሊሆን እንደምገባ በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ መስፍን ደምሴ (ዶ/ር) ተናግረዋል።‎

‎በተለይም ወጣቶች ከፋፋይ ከሆነ አጀንዳ በመውጣት የማህበረሰቡን አንድነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩሩ አስተዳዳሪው በአጽንኦት ተናግረዋል።‎

‎በሚዲያ አጠቃቀም ማህበራዊ መስተጋብራችንን ከሚያዳክሙ የተሳሳተ መረጃ ከማሰራጨት፣ ጭፍን ጥላቻና ያልተረጋገጠን መረጃን ከማጋራት መቆጠብ እንደሚገባ የገለጹት የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስራት በየነ ናቸው።‎

‎ሚዲያዎች ማኅበረሰቡን ሊያስተሳስሩ፣ በዕድገት ጎዳና ሊያራምዱ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መሥራት እንዳለባቸው አቶ አስራት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።‎

‎የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫ ጽህፈት ቤት የሚዲያና የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አይደፈር ሽፈራው፣ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በዞኑ ያሉትን የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ እምቅ ሀብቶች፣ ማህበራዊና ባህላዊ እሴቶች ለዓለም በማስተዋወቅና የማህበረሰቡን ዕድገት የሚጻረሩ ሀሳቦችን በማምከን ወጣቱ ሚናውን እንዲጫወት አስገንዝበዋል።‎

‎የስልጠናው ተሳታፊዎችም በሰጡት አስተያየት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት አፈፃፀም የታዩ መልካም ጅምሮችን በማጠናከርና ውስንነቶችን በማረም በቀጣይ ለተሻለ ሥራ እንዲነሳሱ የሚያዘጋጅ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እንደነበር አንስተዋል።‎

‎ዘጋቢ፡ ውብሸት ኃ/ማርያም – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን