ከአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ደካማ የሆነ የተከላካይ ክፍል ያለው ማንቸስተር ዩናይትድ
የእንግሊዙ ታላቅ ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ በዘንድሮው የውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች ብዙ ግቦችን በማስተናገድ ከአውሮፓ አምስቱ ታላላቅ ሊጎች (ፕሪሚየር ሊግ፣ ላሊጋ፣ ሴሪኤ፣ ቡንደስሊጋ እና ሊግ 1) ደካማው የተከላካይ ክፍል ባለቤት ሆኗል።
ቀያይ ሰይጣኖቹ ትናንት ምሽት በአንፊልድ በሊቨርፑል የደረሰባቸውን አስከፊ የ4-0 ሽንፈት ተከትሎ፣ በውድድር ዘመኑ ያስተናገዱት አጠቃላይ የግብ መጠን 34 ደርሷል።
ይህ አሃዝ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተፎካካሪያቸው ክሪስታል ፓላስ እና በጀርመን ቡንደስሊጋ ከግርጌ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ዩኒየን በርሊን በአንድ ግብ ብልጫ ያለው ነው።
አዲሱ አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ በአንፊልድ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በከባድ ሽንፈት መጀመራቸውን ተከትሎ፣ ዩናይትድ በፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ከግርጌ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ለመቆየት ተገዷል።
ክለቡ በሊጉ ብቻ 23 ግቦችን ያስተናገደ ሲሆን፣ በፕሪሚየር ሊጉ ከእነሱ በላይ ብዙ ግብ የተቆጠረበት ብቸኛው ክለብ 27 ግቦችን ያስተናገደው እና በሰንጠረዡ ግርጌ የሚገኘው ክሪስታል ፓላስ ብቻ ነው።
ይህ አስደንጋጭ አሃዝ የአዲሱን አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ቀጣይ የቤት ስራ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ እና የተከላካይ ክፍሉን በአስቸኳይ ማጠናከር እንደሚገባቸው በግልጽ የሚያሳይ ሆኗል።
ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ
ከአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ደካማ የሆነ የተከላካይ ክፍል ያለው ማንቸስተር ዩናይትድ

More Stories
ዲያጎ ሲሞኔ የስፔን ላሊጋ የምንግዜም የአሸናፊነት ክብረወሰንን በመስበር ታሪክ ሰራ!
ስፖርታዊ ውድድሮች ባህላዊ እሴቶችን ለማጠናከር ያግዛሉ – የአሪ ዞን ባህልና ስፖርት ፅህፈት ቤት
ከ15 ዓመታት በኋላ ማንቸስተር ሲቲን ነጥብ ያስጣለው ፉልሃም