ሪያል ማድሪድ የአርዳ ጉለርን ውል አራዘመ
የስፔኑ ታላቅ ክለብ ሪያል ማድሪድ የቱርካዊውን ኮከብ አርዳ ጉለር ውል እ.ኤ.አ እስከ 2032 ድረስ ማራዘሙን ክለቡ በይፋ አስታውቋል።
በ2023 በ18 ዓመቱ ሪያል ማድሪድን የተቀላቀለው ወጣቱ አማካይ፣ ባለፉት አራት የውድድር ዘመናት በነጩ ማልያ ባሳየው ድንቅ ብቃት የክለቡ ወሳኝ አካል መሆኑን አስመስክሯል።
ጉለር እስካሁን ለሪያል ማድሪድ 126 ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን፣ በዚህ ቆይታውም 5 ታላላቅ ዋንጫዎችን ከፍ አድርጓል።
እነዚህም፦1 የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ፣1 የፊፋ የዓለም ክለቦች ዋንጫ፣1 የአውሮፓ ሱፐር ካፕ፣1 የስፔን ላሊጋ፣1 የስፔን ሱፐር ካፕ ናቸው።
በዓለም አቀፍ መድረክ የቱርክ ብሔራዊ ቡድን ወሳኝ ተጫዋች የሆነው ጉለር፣ እስካሁን ለሀገሩ 38 ጨዋታዎችን ተሰልፎ አከናውኗል።
በተጨማሪም ተጫዋቹ በሜዳ ላይ ለሚያሳየው አስደናቂ እንቅስቃሴ እውቅና በመስጠት፣ ባለፈው መስከረም ወር የ2025-2026 የውድድር ዘመን የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ሽልማትን ማሸነፉ ይታወሳል።
ይህ የረጅም ጊዜ ውል ስምምነት ሪያል ማድሪድ ወጣት ተሰጥኦዎችን በመገንባት የክለቡን የወደፊት ስኬት አስተማማኝ ለማድረግ የያዘውን ራዕይ የሚያጠናክር ነው።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ
ሪያል ማድሪድ የአርዳ ጉለርን ውል አራዘመ

More Stories
“ፖርቹጋል በመሸነፏ ደስተኛ ነኝ!” – የክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ዶሎሬስ አቬይሮ
የፖቸቲኖ ረዳት አሰልጣኞች አስቀድመው ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ አቀኑ
ዴክላን ራይስ በአርሰናል ቤት ለተጨማሪ ዓመታት የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ለመፈረም ተስማማ