ስዊድናዊው የፊት መስመር ተጫዋች ቪክቶር ዮኬሬሽ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ የሚያሳየውን ድንቅ አቋም አጠናክሮ በመቀጠል፣ ስዊድን በኔሽንስ ሊግ ጨዋታ ቦስኒያ እና ሄርዞጎቪናን 3-2 ስታሸንፍ ሁለት ወሳኝ ግቦችን ከመረብ አሳርፏል።
ትናንት ምሽት በስቶክሆልም በተካሄደው በዚህ ጨዋታ፣ የ28 ዓመቱ አጥቂ ከእረፍት በፊት ያስቆጠራቸው ሁለት የፍፁም ቅጣት ምት ግቦች የግራሃም ፖተር ቡድን የምድብ B3 የበላይነትን እንዲቆናጠጥ እና ወደ ኔሽንስ ሊግ ከፍተኛው እርከን (League A) እንዲያድግ አስችለውታል።
ዮኬሬሽ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ስዊድን ባደረገቻቸው አምስት የኔሽንስ ሊግ ጨዋታዎች በሁሉም ላይ ግብ በማስቆጠር አስገራሚ ሪከርድ ይዟል።
በአጠቃላይ ደግሞ በ8 ተከታታይ ጨዋታዎች የኔሽንስ ሊግ ጨዋታዎች ጎል በማስቆጠር በታሪክ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።አጥቂው በነዚህ ጨዋታዎች 12 ግቦችን ከመረብ አሳርፏል።
ይሁን እንጂ፣ ተጫዋቹ በሀገሩ ማልያ የሚያሳየው ይህ አስፈሪ የግብ አዳኝነት ብቃት በክለብ ደረጃ ከሚገኝበት ወቅታዊ አቋም ጋር ፍጹም ተቃራኒ ሆኖ ታይቷል።
ለእንግሊዙ ክለብ አርሰናል የሚጫወተው ዮኬሬሽ በዘንድሮው የውድድር ዓመት በ14 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ማስቆጠር የቻለው ሁለት ግቦችን ብቻ ሲሆን፣ በፕሪሚየር ሊጉ በቋሚነት የጀመረውም በአንድ ጨዋታ ላይ ብቻ ነው።
ይህም በክለብ ደረጃ የመሰለፍ ዕድልና የግብ ድርቅ ቢገጥመውም፣ ለሀገሩ ሲጫወት ግን ዋነኛ የግብ ምንጭ መሆኑን በድጋሚ ያረጋገጠበት ምሽት ሆኗል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
የትምህርት ጥራት ችግሮችን በተገቢው መንገድ ለመቅረፍና በዘርፉ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት ሁሉም በቅንጅት መሥራት እንዳለበት ተጠቆመ
በግብርናው ዘርፍ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት ወደ ተግባር መገባቱ ተገለፀ
የምርት አሰባሰብ ዘመቻው በተቀናጀ መንገድ እንዲካሄድ ጥሪ ቀረበ