28ኛው የጤናው ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ በሆሳዕና ከተማ መካሄድ ጀምሯል
በዕለቱ ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) 28ኛውን የጤናውን ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ በማስመልከት በሆሳዕና ከተማ የተዘጋጀውን ኤግዚቢሽን መርቀዉ ከፍተዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) እና የኢፌዲሪ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ኤግዚቢሽኑን በጋራ መርቀው ለተመልካች ክፍት አድርገዋል።
በኤግዚቢሽኑ ከፌደራል፣ ከክልሎች እና ከከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ተቋማት በጤናው ዘርፍ ያላቸውን አቅም እያሳዩ ነው።
ዘጋቢ፡ ብሩክ አማረ

More Stories
የእንሰት ተክል ያለውን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ በተመለከተ የተለያዩ የጥናትና ምርምር ሥራዎች መሰራታቸውን የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ገለፀ
በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ውብ የተፈጥሮ እና ሰፊ የባህል ሀብቶችን በአግባቡ በማልማት ለክልሉ ብሎም ለሀገር እድገትና ብልጽግና ማዋል ይገባል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ካሣሁን ተናገሩ
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ስናከብር ብዝሀዊ ማንነትን በማረጋገጥና ሀገራዊ አንድነትን በማስከበር ሊሆን ይገባል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት