የእንሰት ተክል ያለውን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ በተመለከተ የተለያዩ የጥናትና ምርምር ሥራዎች መሰራታቸውን የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ገለፀ
የእንሰት ተክል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የስራ እድል ለመፍጠር እና ያለውን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ በተመለከተ የተለያዩ የምርምር ሥራዎችን መሰራታቸውን የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ገለፀ፡፡
3ኛዉ የአለም አቀፍ የእንሰት ሲንፖዝዬም በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ ይገኛል።
በእንሰት ተክል ላይ የተገኙ የምርምር ውጤቶች በግብርናዉ ዘርፍ የተጀመረውን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ሚናዉ የጎላ እንደሆነም በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የምርምር እና የማህበረሰብ አገልገሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተክሉ ወጋዬሁ ተናገረዋል።
ዶ/ር ወጋዬሁ አክለውም የእንሰትን ተክል በምርምር በመደገፍ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ እና ከባህላዊ አዘገጃጀት ወደ ዘመናዊ በመቀየር ለ100 ሺህ የሚሆኑ ሴቶች በዘርፉ የስራ እድል እንደተፈጠረ አስረድተዋል።
የእንሰት ተክል በተለይም በደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢዎች ላይ የዕለት ተዕለት ምግብ ከመሆኑም በላይ ተክሉ ድርቅን የመቋቋም አቅሙ ከፍተኛ እንደሆነም ተመላክቷል።
የአርባምንጭ ዪኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኢ/ር አብደላ ከማል በበኩላቸው፤ በባህላዊ መንገድ እንሰት የሚዘጋጅበት መንገድ የጊዜ፣ የጉልበት፣ የንጽህና እና የብክነት ሂደቶችን ለመቅረፍ በዘርፉ የምርምርና የጥናት ውጤቶችን በመጠቀም ለህብረተሰቡ ምርቱን ከማሳደግ አኳያ መጠነ ሰፊ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ከ20 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ የእንሰት ተክልን በምግብነት እንደሚጠቀሙ ገልፀው፤ ዩኒቨርስቲው የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችን በምርምር በመደገፍ መስራት ዋነኛ ተግባሩ እንደሆነም ገልጸዋል።
የእንሰት ተክልን በተመለከተ ከተለያዩ የአለም አቀፍ ተመራማሪዎች እና አጋሮች ጋር በጋራ በመቀናጀት የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
በመድረኩ የተለያዩ አለም አቀፍ ተመራማሪዎች፣ የዩኒቨርስቲ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፡ ስምረት አስማማው – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ውብ የተፈጥሮ እና ሰፊ የባህል ሀብቶችን በአግባቡ በማልማት ለክልሉ ብሎም ለሀገር እድገትና ብልጽግና ማዋል ይገባል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ካሣሁን ተናገሩ
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ስናከብር ብዝሀዊ ማንነትን በማረጋገጥና ሀገራዊ አንድነትን በማስከበር ሊሆን ይገባል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እና በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በጋራ በTAAT- II wheat compact ፕሮጀክት ድጋፍ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀዲያ ዞን ሚሻ ወረዳ በቡዕማ ቀበሌ የተከናወነ ማህበረሰብ ዓቀፍ የስንዴ ዘር ብዜት ማሳ ላይ ብሔራዊ የአርሶ አደሮች የመስክ በዓል እየተከበረ ይገኛል