የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ስናከብር ብዝሀዊ ማንነትን በማረጋገጥና ሀገራዊ አንድነትን በማስከበር ሊሆን ይገባል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ስናከብር ብዝሀዊ ማንነትን በማረጋገጥና ሀገራዊ አንድነትን በማስከበር መሆን እንዳለበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አዳማ ትምጳኤ ተናገሩ፡፡
21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል ክልላዊ የማብሰሪያ እና የአሰልጣኞች ስልጠና መድረክ በኮንሶ ካራት ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በዓሉ “የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በብዝሀነት የደመቀች፣ በምክክር የፀናች፣ ስልጡን ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበርም ተመላክቷል።
በመርሀ ግብሩ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አዳማ ትምጳኤ፤ 21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓልን ስናከብር ብዝሀዊ ማንነትን በማረጋገጥና ሀገራዊ አንድነትን በማስከበር ሊሆን ይገባል ብለዋል።
በዓሉ ባህሎችንና ትሩፋቶችን ከማስተዋወቅ ባለፈ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ እየሆነ መምጣቱን አውስተው፤ በሀገራችን የቱሪዝም መዳረሻዎች በስፋት በመገንባታቸው ምክንያት መጠነ-ሰፊ ለውጦች እየተስተዋሉ ይገኛሉም ብለዋል።
ሀገራችን ለአፍሪካ ተምሳሌት የሚሆኑ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ በማድረግ እድገቷ ከፍ እያለ መምጣቱን የተናገሩት አቶ አዳማ ትምጳዬ፤ ይህንንም በዓል በመደመር መንግስት እሳቤ የህዝብን ጥቅም በሚያስከብር መልኩ እንደሚከበር ገልፀዋል።
በመርሀ ግብሩ በክልሉ ከሚገኙ ዞኖች እና ሪጂዮፖሊ ከተሞች የተውጣጡ አፈ-ጉባኤዎችና ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በመድረኩ በዓሉን በማስመልከት መሪ ዕቅድ እና በብዝሀነት አስተዳደር ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ ሲሆን በባህል ፌስቲባልና ኤግዚቢሽን፣ በውይይቶች፣ ደም ልገሳ፣ የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት በማደስ፣ በስፖርታዊ ጨዋታዎች እና በተለያዩ ኩነቶች እንደሚከበር ተገልጿል።
ዘጋቢ፡ ተመኙህ ገረሱ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
የእንሰት ተክል ያለውን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ በተመለከተ የተለያዩ የጥናትና ምርምር ሥራዎች መሰራታቸውን የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ገለፀ
በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ውብ የተፈጥሮ እና ሰፊ የባህል ሀብቶችን በአግባቡ በማልማት ለክልሉ ብሎም ለሀገር እድገትና ብልጽግና ማዋል ይገባል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ካሣሁን ተናገሩ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እና በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በጋራ በTAAT- II wheat compact ፕሮጀክት ድጋፍ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀዲያ ዞን ሚሻ ወረዳ በቡዕማ ቀበሌ የተከናወነ ማህበረሰብ ዓቀፍ የስንዴ ዘር ብዜት ማሳ ላይ ብሔራዊ የአርሶ አደሮች የመስክ በዓል እየተከበረ ይገኛል