በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ውብ የተፈጥሮ እና ሰፊ የባህል ሀብቶችን በአግባቡ በማልማት ለክልሉ ብሎም ለሀገር እድገትና ብልጽግና ማዋል ይገባል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ካሣሁን ተናገሩ
ኃላፊው ይህንን ያሉት፥ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጸጻም እየገመገመ ይገኛል።
በጉባኤው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ካሣሁን፤ ተሳታፊዎችንና ጥሪ የተደረገላቸውን እንግዶች “እንኳን በደህና መጣችሁ” በማለት የጉባዔውን መጀመር በይፋ አብስረዋል።
በመቀጠልም በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ውብ የተፈጥሮ መልክዓ ምድር፣ ሰፊ የደን ሀብቶችንና እምቅ የባህል ሀብቶችን በአግባቡ በማልማት ለክልሉ እና ለሀገር እድገትና ብልጽግና ማዋል ይገባል ብለዋል።
ለዚህም ቢሮው ባለድርሻ አካላትንና ህብረተሰቡን በማስተባበር በቱሪዝም ዘርፍ ባደረገው ተከታታይ ጥረት በአገር አቀፍ አንደኛ ደረጃ ውጤት ማስመዝገቡን አስረድተዋል።
በጉባኤው በ2018 በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ ያሉ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ መስህቦችን ከማልማት አኳያ በክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ በኩል የተሰሩ ሥራዎች ዕቅድ አፈፃጸም በሚመለከት ጠቋሚ ሪፖርት በቢሮው የልማት ዕቅድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እሸቱ ኢምቶ በኩል ቀርቧል።
የዱር እንስሳትን የመጠበቅ ሥራን በተመለከተም አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል፤ ለዚህም በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎችና ስካውቶች አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነም ተገልጿል።
በክልሉ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦችን የዘመን መለወጫ ባህላዊ በዓላትን ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ዓለም ከማስተዋወቅ አንፃር ሰፊ ሥራዎች እንደተሰሩም ሪፖርቱ አትቷል።
እንደ ሪፖርቱ ገለጻ፥ የግሉ ዘርፍ ኢንቨስትመንት ማስፋፋትና የፋይናንስ አቅም ለማጎልበት በተከናወኑ ሥራዎችም አበረታች ውጤት ታይቷል።
የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ፍሰት በማሳደግ ለክልሉ የውስጥ ገቢን ለማመንጨት ታቅዶ በተሰራ ሥራም የቱሪዝም ፕሮሞሽንና ግብይት ሥራዎችን ማጎልበት ስለመቻሉም በሪፖርቱ ተብራርቷል።
በመድረኩም የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ሰነድ በዝርዝር እየቀረበ ይገኛል።
በጉባኤው የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፀሐይ ደርጫን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ከተለያዩ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የመጡ የዘርፉ ባለሙያዎችና አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በጉባኤው ላይ ተገኝተዋል።
ዘጋቢ: ፍቃዱ ማቴዎስ – ከዋካ ቅርንጫፍ
በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ውብ የተፈጥሮ እና ሰፊ የባህል ሀብቶችን በአግባቡ በማልማት ለክልሉ ብሎም ለሀገር እድገትና ብልጽግና ማዋል ይገባል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ካሣሁን ተናገሩ

More Stories
የእንሰት ተክል ያለውን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ በተመለከተ የተለያዩ የጥናትና ምርምር ሥራዎች መሰራታቸውን የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ገለፀ
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ስናከብር ብዝሀዊ ማንነትን በማረጋገጥና ሀገራዊ አንድነትን በማስከበር ሊሆን ይገባል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እና በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በጋራ በTAAT- II wheat compact ፕሮጀክት ድጋፍ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀዲያ ዞን ሚሻ ወረዳ በቡዕማ ቀበሌ የተከናወነ ማህበረሰብ ዓቀፍ የስንዴ ዘር ብዜት ማሳ ላይ ብሔራዊ የአርሶ አደሮች የመስክ በዓል እየተከበረ ይገኛል