ወላይታ ድቻ ወልዋሎን በማሸነፍ ተከታታይ ድል አስመዘገበ
በ5ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ወላይታ ድቻ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲን 2ለ0 በማሸነፍ ሁለተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል።
በሀላባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የጦና ንቦችን የድል ግቦችን መሳይ ሰለሞን እና ሐሰን ሁሴን ከመረብ አሳርፈዋል።
አጥቂው መሳይ ሰለሞን በዚህ ዓመት 5ኛ የሊግ ጎሉን በማስቆጠር ከአንተነህ ተፈራ ጋር በእኩል የግብ መጠን የከፍተኛ ግብ አግቢነቱን ይመራል።
ወላይታ ድቻ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 8 በማድረስ 3ኛ ደረጃን መያዝ ችሏል።
ሦስት ተስተካካይ ጨዋታዎች ያሉት ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ አንድ ነጥብ ይዞ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ሀዋሳ ከተማ ጋሞ ጬንቻን በማሸነፍ በዚህ ዓመት የመጀመሪያ ድሉን አሳካ
የኤዝሪ ኮንሳ እና ጋብሬል ማጋሌሽ ድንቅ ጥምረት በአርሰናል
የአርሰናል እና ሊቨርፑል ተጠባቂ ጨዋታ!