ቼልሲ ማንቸስተር ዩናይትድን በመርታት ወደ አሸናፊነት ተመለሰ

ቼልሲ ማንቸስተር ዩናይትድን በመርታት ወደ አሸናፊነት ተመለሰ

በተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሃ-ግብር ቼልሲ በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጅ ማንቸስተር ዩናይትድን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በመርታት የድል ጉዞውን አድሷል።

በሁለተኛው አጋማሽ በነበረው የጨዋታ የበላይነት ቼልሲን አሸናፊ ያደረጉትን ግቦች ሞርጋን ሮጀርስ እና ኮል ፓልመር በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፈዋል።

ጨዋታው ለቀያይ ሰይጣኖቹ የበለጠ ከባድ የሆነው ተከላካዩ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በሰራው ጥፋት በሁለት ቢጫ (ቀይ) ካርድ ከሜዳ ከተሰናበተ በኋላ ነበር።

ማንቸስተር ዩናይትድ ከዚህ ሽንፈት ጋር ተያይዞ ከ65 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሁሉም ውድድሮች በሦስት ተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈትን አስተናግዷል።

በተጨማሪም እ.ኤ.አ ከ1988 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በ9 ተከታታይ ጨዋታዎች ማሸነፍ ሳይችል ቀርቶ ከባድ የታሪክ ጠባሳዎች ተደቅነውበታል።

ለሰማያዊዎቹ የፍፁም ቅጣት ምቷን ጎል ያስቆጠረው ኮል ፓልመር፡ በቼልሲ ማሊያ በ105 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች 50ኛ ጎሉን ማስመዝገብ ችሏል።

በክለቡ ታሪክ 50 ግቦችን ከፓልመር ባነሰ ጨዋታ ያስቆጠሩት ጂሚ ፍሎይድ ሀሰልባይንክ 84 ጨዋታዎች እና ዲያጎ ኮስታ 85 ጨዋታዎች ብቻ ናቸው።

በአሰልጣኝ ሻቪ አሎንሶ የሚመራው ቼልሲ በዚህ ዓመት በሊጉ በሦስት ጨዋታዎች ግብ ሳይቆጠርበት ከሜዳ መውጣት የቻለ ሲሆን፡ በውጤቱም ነጥቡን ወደ 16 ከፍ በማድረግ ደረጃውን ወደ 4ኛ አሻሽሏል።

ማንቸስተር ዩናይትድ በአንፃሩ የውድድር ዘመኑን 4ኛ የሊግ ሽንፈት አስተናግዶ በ7 ነጥብ ከወራጅ ቀጠናው በ1 ነጥብ ብቻ ርቆ 16ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ