ማንችስተር ዩናይትድ ፈርሚን ሎፔዝን ለማስፈረም ፍላጎት ማሳየቱ ተገለጸ
ማንችስተር ዩናይትድ መጪው የጥር የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት ሲከፈት የባርሴሎናውን አማካኝ ፈርሚን ሎፔዝን ወደ ኦልድትራፎርድ ለማምጣት ፍላጎት ማሳየቱ ተዘግቧል።
የእንግሊዙ “ዴይሊ ሜይል” ጋዜጣ ባወጣው መረጃ መሠረት የ23 ዓመቱ ስፔናዊ የፊት መስመር አማካኝ ፈርሚን ሎፔዝ በካታላኑ ክለብ ባርሴሎና 70 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ዋጋ ተለጥፎበታል።
ሆኖም ቀያይ ሰይጣኖቹ ተጫዋቹን ለማስፈረም በሚያደርጉት ጥረት ከባድ ፉክክር ይጠብቃቸዋል።
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ እና የፈረንሳዩ ፒኤስጂ የዚህን የአጥቂ አማካይ ተጫዋች የዝውውር ሁኔታን በቅርበት እየተከታተሉ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።
ማንችስተር ዩናይትድ በጥር ወር በሚከፈተው የዝውውር መስኮት ወደ ተጫዋች ዝውውር ገበያው ለማተኮር የተገደደው፣ በአጥቂው ቤንጃሚን ሼስኮ ላይ በተደጋጋሚ የሚያጋጥመው የጉዳት ችግር የማጥቃት ኃይሉን በመፈተኑ ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል።
በተጨማሪም ክለቡ የማጥቃት አማራጩን ለማስፋት የሊድስ ዩናይትዱን አጥቂ ዶሚኒክ ካልቨርት-ሊዊንን በዕጩነት ይዞ እንደሚገኝ የዴይሊ ሜይል ዘገባ ያመላክታል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ሃሪ ኬን ኪሊያን ምባፔን በ28 ነጥብ ብቻ በመበለጥ ባሎንዶሩን ማሸነፉ ይፋ ሆነ
ካርሎስ ቴቬዝ ከማንቼስተር ዩናይትድ ወደ ማንቼስተር ሲቲ ያደረገው ዝውውር በበቀል ላይ የተመሰረተ እንደነበር ተናገረ
ባየር ሙኒክ ለባሎንዶር አሸናፊው ሃሪ ኬን የጀግና አቀባበል አደረገ