የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጂጌ (ዶ/ር) በተገኙበት የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ የመደመር መንግስት ምስረታን ተከትሎ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2019 ዕቅድ ፈፃሚ ማዘጋጃ መድረክ በአርባምንጭ ተጀመረ
በመርሀ ግብሩ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2019 የመቶ ቀን እቅድ እና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ከተመረጡ የባለድርሻ ተቋማትና የመምሪያ ኃላፊዎች ጋር የግብ ስምምነትም ይደረጋል።
በመርሀ ግብሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጂጌ (ዶ/ር)፣ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ካሰች ኤሊያስ፣ የክልሉ ዋና የመንግሥት ተጠሪ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር)፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ደምሴ አድማሱ(ዶ/ር)፣ የስራ፣ ስራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር ጨምሮ የተመረጡ ባለድርሻ ተቋማት ተወካዮች፣ የመምሪያ ኃላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል።
ዘጋቢ፡ ተመኙህ ገረሱ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጂጌ (ዶ/ር) በተገኙበት የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ የመደመር መንግስት ምስረታን ተከትሎ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2019 ዕቅድ ፈፃሚ ማዘጋጃ መድረክ በአርባምንጭ ተጀመረ

More Stories
ግብርናን በማሻገር የአርሶአደሩን ኑሮ ለማሻሻል የተጀመሩ የኢኒሼቲቭ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ
የመደመር መንግስት ለጤናው ዘርፍ ትኩረት በመስጠቱ በ2018 በጀት አመት በልዩ ወረዳው ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል – የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ
ጠንካራ ተቋም በመመስረት ህዝብና መንግስት ከሴክተሩ የሚጠብቁትን ውጤት ለማስመዝገብ እንሰራለን – የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ