መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት እውን ማድረግ እንዲቻል ተመራቂ ተማሪዎች በተመረቁበት የሙያ መስክ ማህበረሰቡን በታማኝነት ሊያገለግሉ ይገባል ሲሉ አቶ አንነህ ፈቃዱ ገለጹ
የሆሳዕና መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በክረምት መርሃ ግብር በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1ሺህ 224 ተማሪዎች አስመርቋል።
በምረቃ መርሀ-ግብሩ ላይ የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ የቅድመ መደበኛ ደረጃ ትምህርት የህፃናት የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወሰንበት የህዝብ አገልግሎት እንደመሆኑ ትልቅ ኃላፊነትን የሚሻ መሆኑን ገልፀዋል።
የትምህርት ሽፋን ተደራሽነትን ከጥራት ጋር በማጣመር መስራት ወሳኝ ነው ያሉት አቶ አንተነህ ክልሉ ከተመሰረተ ወዲህ እንደ ቢሮው የትምህርት ዘርፍን ማሳደግና ማዘመን ላይ በአትኩሮት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት እውን ማድረግ እንዲቻል ተመራቂ ተማሪዎች በተመረቁበት የሙያ መስክ ማህበረሰቡን በታማኝነት ሊያገለግሉ እንደሚገባ ጠቁመው እንደ ክልሉ ትምህርት ቢሮ የጥራት ክፍተቶችን ለመሙላት ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተከናውነው በዚሁም በሀገራዊም ሆነ ክልላዊ ፈተናዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል ነው ያሉት ።
የክልሉን ቋንቋ ብዝኃነት ማሳደግ እንዲቻል በትምህርት ተቋማት በየብሔረሰብ የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች የማሰልጠን ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚነኙ በመግለጽ
ተመራቂዎች የእድሜ ልክ ተማሪ በመሆን፣ተማኝና ርህሩህ አገልጋይ እንዲሁም በየተሰማሩበት ዘርፍ የሠላም፣ የመቻቻልና የጋራ እድገት አጋር በመሆን ለሀገሪቱ ዘላቂ ሠላምና ልማት የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
አቶ አንተነህ አክለውም ተመራቂዎች ሙያቸውን ስራ ለማግኘት ብቻ ሳይሆን ስራ በመፍጠር ለህዝብ አገልጋይነት ዓላማ ሊጠቀሙ እንደሚገባ በመጠቆም በከፍተኛ ውጤት የተመረቁ ተማሪዎች ከወዲሁ የድፕሎማ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ትምህርት ቢሮው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ገልፀዋል።
የሆሳዕና መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ዲን አባይነህ ኤርጎጎ (ዶ/ር) በበኩላቸው በሀገራችን በሚደረጉ ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴዎች የትምህርት ዘርፍ ትልቅ አበርክቶ አለው ብለዋል።
የመምህርነት ሙያ ሁሉ ዐቀፍ ሙያ ነው ያሉት ዲኑ በኮሌጁ ብቁ ዜጎችን ማፍራት እንዲቻል ለመምህራን የስራ ላይ ስልጠናዎችን ከመስጠት ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
ሰልጣኝ መምህራኑ የነገዋ ሀገር ባለቤት የሆኑ የህፃናት አስተማሪዎች እንደመሆናቸው ፥ ጨወታን መሠረት ያደረገ የማስተማሪያ ስነ ዘዴን በተግባራዊ ልምምድ በማስደገፍ እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።
የኮሌጁ አካዳሚክ ምክትል ዲን ደስታ በቀለ (ዶ/ር) በበኩላቸው የቅድመ መደበኛ ደረጃ መምህርነት የዛሬን ህፃናት መንገድ በመምራት የነገ ትውልድ የሚገነባበት ቁልፍ ኃላፊነት ነው ብለዋል።
ያነጋገርናቸው ተመራቂ ተማሪዎችም የኮሌጁን የትምህርት ቆይታ ጊዜ በስኬት በማጠናቀቃቸው ደስተኞች መሆናቸውን ጠቁመው በሰለጠኑበት የሙያ መስክ የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ዘጋቢ: አማኑኤል አጤቦ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማንና ካቢኔያቸው ለሕዝባዊ ውይይት ሚዛን አማን ከተማ ገቡ
በካፋ ዞን “ማንሰራራት ለዞናችን ከፍታ” በሚል መሪ ቃል የመደመር መንግስት የትውውቅ መድረክ እየተካሄደ ነው
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ አስፈፃሚ ተቋማት የህዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለሚያረጋግጡ ተግባራት ትኩረት ሊሰጡ ይገባል – አፈ ጉባኤ ካሰች ኤሊያስ