ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማንና ካቢኔያቸው ለሕዝባዊ ውይይት ሚዛን አማን ከተማ ገቡ

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማንና ካቢኔያቸው ለሕዝባዊ ውይይት ሚዛን አማን ከተማ ገቡ

እንግዶቹ ወደ ዞኑ ሲደርሱ ዋቻማጂ እና በርዕሰ መስተዳድሩ የትውልድ ስፍራ ሰሜን ቤንች ወረዳ ያሊ ቀበሌ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

መድረኩ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ መነሻ የመንግስት ምስረታ መደረጉን ተከትሎ ከክልሉ ህዝብ ጋር ትውውቅ ለማድረግና በጋራ ጉዳዮች ላይ ግልጸኝነትና መግባባትን ለመፍጠር ያለመ ነው።

ይሄው መርሀ ግብር በክልሉ ዳውሮ፣ ኮንታ እና ካፋ ዞኖች በተመሳሳይ ሁኔታ መካሄዱ ይታወሳል።

አቶ ፍቅሬ አማን ተወልደው ባደጉበት ያሊ ቀበሌና አከባቢው ተውጣጥው ደማቅ አቀባበል ላደረጉ ወገኖች ምስጋና አቅርበዋል።

“እኔና ወንድሞቼ ይህንን ክልል ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ እንዲናደርስ ዕድል ስለሰጣችሁን እናከብራችኋለን” ያሉ ሲሆን ቃላችን ጠብቀን አናገለግላlን ብለዋል።

በቤንች ሸኮ ዞን ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር በሚካሄደው የትውውቅና የሕዝባዊ ውይይት መርሐ ግብር ለማካሄድ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ሚዛን አማን ከተማ ሲደርሱም በርካታ የከተማው ነዋሪዎችና አመራሮች በባህላዊ ጭፈራ የታጀበ አቀባበል አድርገዋል።

መርሐ ግብሩ የሕዝቡን የልማት፣ የሰላምና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በቀጥታ ለማዳመጥ፣ በጋራ ለመመካከርና ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችን ለመቀየስ ትልቅ ትርጉም ያለው ነው።

ውይይቱም የቤንች ሸኮ ዞን ማኅበረሰብ ክፍሎች የሚያነሷቸውን ቅድሚያ የሚሹ ጥያቄዎች በመለየትና ለመፍታት የሚያስችሉ የጋራ የሥራ አቅጣጫዎችን በመወያየት በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ያለውን የትብብር መንፈስ ለማጠናከር የሚያስችል ነው።

ቤንች ሸኮ ዞን በግብርና፣ በቱሪዝም፣ በደንና በተፈጥሮ ሀብት ያለው እምቅ አቅም ለክልሉ ልማትና ለሕዝቡ ተጠቃሚነት ትልቅ ዕድል ይዞ ይገኛል።

ይህንን ጸጋ በአግባቡ በማልማትና ወደ ተጨባጭ የልማት ውጤት በመቀየር የሥራ ዕድልን ለማስፋትና የሕዝቡን ኑሮ ለማሻሻል በጋራ መሥራት የውይይቱ ቁልፍ አቅጣጫ ይሆናል።

ነገ ጥቅምት 15 ቀን 2019 ዓመተ ምህረት በሚዛን አማን ከተማ ታላቅ ትርጉም ያለው ሕዝባዊ ውውይይት ርዕሰ መስተዳድሩ በተገኙበት እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

ዘጋቢ፡ አሳምነው አትርሳው – ከቦንጋ ማስተባበሪያ