በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ አስፈፃሚ ተቋማት የህዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለሚያረጋግጡ ተግባራት ትኩረት ሊሰጡ ይገባል – አፈ ጉባኤ ካሰች ኤሊያስ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት በ2019 በጀት ዓመት ከክልል አስፈፃሚ ተቋማት ኃላፊዎች፣ ከዞንና ሪጅዮፖሊስ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች ጋር ዓመታዊ የዕቅድ ውል ስምምነትና ኦሬንቴሽን መድረክ በአርባምንጭ አድርጓል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወሮ ካሰች ኤልያስ፤ መድረኩ ምክር ቤቶች የተሰጣቸውን ሀላፊነት፣ ስልጣንና ተግባር ከመፈፀም እና ከማስፈፀም ባሻገር የቁጥጥርና የክትትል ስራዎችን ለማከናወን በማሰብ መዘጋጀቱን አብራርተዋል።
ምክር ቤቶች የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ክትትልና ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር የህዝብ ውክልናን መወጣት፣ ቅሬታ በማዳመጥ ከተቋማት ጋር በቅንጅት ከመስራት ባሻገር አሁናዊ እቅዶቻችንን ለማሳካት በቅንጅት መስራት ይጠበቅብናል ሲሉም አክለዋል።
ቅሬታ የሚስተዋልባቸው ተቋማትን በመለየት አስተያየት መስጫ መድረኮችን በማዘጋጀትና በማወያየት ችግሮች እንዲቀረፉ የማድረግ ስራ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራም አመላክተዋል።
በመድረኩ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የህግ ጉዳዮች አማካሪ ወ/ሮ መስከረም ወልደ ማሪያም አጠቃላይ የምክር ቤቱን ተግባራት አስመልክቶ ገለፃ አድርገዋል።
በተለይም ከመልካም አስተዳደር ፤ አዋጆችን ከመተግበር፣ ከኢንቨስትመንት እና ከተማ ልማት፣ የተቋም ግንባታ፣ ከህዝብ የልማትና መልካም አስተዳደር እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
የክልል አስፈፃሚ ተቋማት ኃላፊዎች፣ የዞንና ሪጅዮፖሊስ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች የተወጣጡ አመራሮች በመርሀ ግብሩ ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ተመኙህ ገረሱ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት እውን ማድረግ እንዲቻል ተመራቂ ተማሪዎች በተመረቁበት የሙያ መስክ ማህበረሰቡን በታማኝነት ሊያገለግሉ ይገባል ሲሉ አቶ አንነህ ፈቃዱ ገለጹ
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማንና ካቢኔያቸው ለሕዝባዊ ውይይት ሚዛን አማን ከተማ ገቡ
በካፋ ዞን “ማንሰራራት ለዞናችን ከፍታ” በሚል መሪ ቃል የመደመር መንግስት የትውውቅ መድረክ እየተካሄደ ነው