“ጊፋታ” ህብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚያጠናክር በዓል መሆኑ ተገለፀ
“የትወልድ ቅርስ እንጠብቅ፤ የጊፋታን ውርስ እናስቀጥል” በሚል መሪ ቃል የወላይታ ባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና የመንግሥት ተጠሪ እና የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረመስቀል ጫላ፤ የሰላም ተምሳሌት በሆነው በጊፋታ በዓል በጥንት አባቶቻችን ሲከበር የነበረ እና አሁን የወላይታ በዓል ብቻ ሳይሆን የዓለም ቅርስ ሆኖ በዩኔስኮ በመመዝገቡ የሁሉም በዓል ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በርካታ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ቅርሶች ባለቤት ነው ሲሉ በመግለጽ ጊፋታ ከማይዳሰሱ ቅርሶች አንዱ እንደሆነ ተናግረዋል።
የሰላም፣ የዕርቅ እና ህብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚያጠናክር በዓል እንደሆነ በመጥቀስ በዓሉ በሁለንተናዊ ዘርፍ ጠቀሚታ ያለው መሆኑን ተናግረዋል።
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ እንደገለጹት፤ “ጊፋታ” ለበርካታ ዓመታት የተደረገው የልፋት ውጤት ፍሬ አፍርቶ በዩኔስኮ መመዝገቡ እና ለህዝባችንም ልዩ ጥቅም የሚያስገኝ እና ባህላችን በዓለም ደረጃ እንዲታወቅ ያደረገ ነው።
በዓሉን ለማክበር የመጡ እንግዶችን በተለመደ የእንግዳ አቀባበል ባህል ህብረተሰቡ እንዲቀበል አሳስበዋል።
የወላይታ ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ስምዖን ስላሎ፤ የጊፋታ በዓል በዩኔስኮ በተመዘገበበት በመጀመሪያው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከበር መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው ተናግረዋል።
እጅ ለእጅ በመያያዝ ባህላችን እና ቋንቋችንን የማሳደግ ኃላፊነት ይኖርብናልም ብለዋል።
ዘጋቢ፡ ፈቃዱ ማትዮስ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
አርሰናል የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ሽንፈት አስተናገደ!
ብዝኃ ህይወትን ቀጣይነት ባለው መንገድ በማልማትና በመንከባከብ ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ ይገባል – አቶ ተፈሪ አባተ
ቢሮው በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ልኬት ስራ በማጠናቀቅ የይዞታ ማረጋገጫ ለአርሶአደሮች አስረከበ