የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ቴክኖሎጂን በመቅዳት፣ በማሻሻልና በመፍጠር ለሀገራዊ ዕድገት ከፍተኛ አበርክቶ አላቸዉ – የክልሉ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰፋ ደቼ

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ቴክኖሎጂን በመቅዳት፣ በማሻሻልና በመፍጠር ለሀገራዊ ዕድገት ከፍተኛ አበርክቶ አላቸዉ – የክልሉ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰፋ ደቼ

ሀዋሳ፡ መስከረም 07/2019 ዓ.ም (ደሬቴድ) የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ቴክኖሎጂን በመቅዳት፣ በማሻሻልና በመፍጠር ለሀገራዊ ዕድገት ከፍተኛ አበርክቶ እንዳላቸዉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰፋ ደቼ ገለፁ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ሴክቶሪያል ጉባኤዉን በዱራሜ ከተማ እያካሄደ ነዉ።

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በዕዉቀት፣ ክህሎትና ፈጠራ የተገነባ የሰዉ ኃይል ለማፍራት ትልቅ መሰረት መሆናቸዉን የጠቀሱት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰፋ ደቼ፤ በክልሉ የሚገኙ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ቴክኖሎጂን በመቅዳት በማሻሻልና በመፍጠር በርካታ ተግባራትን እያከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

ስልጠናዎቹ ሰራተኛን መፍጠር ሳይሆን ስራን የሚፈጥሩና ለሌሎች ዜጎችም የስራ ዕድል የሚፈጥሩ ሰልጣኞችን ማፍራት መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊዉ፤ ተቋማቱን ከኢንዱስትሪዎች ጋር ማስተሳሰር እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡

በ2019 በጀት ዓመት ከ1 ሺህ 7 መቶ በላይ ሰልጣኞችን ለመቀበል ከታቀደዉ 1 ሺህ 6 መቶ 33 ሰልጣኞችን መቀበል መቻሉን ተናግረዋል፡፡

አዲስ ሰልጣኝ ቅበላ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

በተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት በስልጠና ጥራት የተሻለ ተግባር ተፈጽሟል ያሉት ኃላፊዉ፤ ከሰልጣኞችና ኢንተርፕራይዞች ምዘና ጋር ያሉ ጉድለቶችን ማረም እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ዘጋቢ፡ ድልነሳዉ ታደሰ