ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመቆጣጠር በቅድመ ምርመራ ስራዎች ላይ ትኩሩት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን በሀላባ ዞን የቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽህፈት ቤት አስታወቀ
የቁልቶ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰይፈዲን ቱልሳ እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት እየተባባሰ የመጣውን የወባ ወረርሽኝ ለመከላከል በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል።
በዚህ ወቅት የወባ ትንኝ እንዲራባ ምቹ የሆኑና ውሃ ያቆሩ ቦዮችን በማፋሰስ እንዲሁም ጉድጓዶችን የመድፈን ስራዎችን ከመስራት ባለፈ የኬሚካል ርጭትና ሌሎችንም የመከላከያ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ መሆኑን ገልፀዋል።
አቶ ሰይፈዲን አክለውም፤ ሌሎችንም ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመቆጣጠር በቅድመ ምርመራ ላይ ትኩሩት በመስጠት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
በከተማ አስተዳደሩ በሁሉም ቀበሌያት የማህፀን በር ጫፍ ከንሳር፣ የደም ግፊት፣ ስኳርና መሰል በሽታዏችን በዘመቻ መልክ ምርመራ በማድረግ የመለየት ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በቁሊቶ ከተማ ጤና ጣቢያ ለነፍሳጡር እናቶች ብቻ የላብራቶሪ ምርመራ አገልግሎት የሚሰጥበት ማዕካል ተገንብቶ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑንም ኃላፊው አያይዘው ገልፀዋል።
ባለፈው በጀት ዓመት ለ184 እናቶች የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ቅድመ ምርመራ በማድረግና የህክምና አገልግሎት በመስጠት ከሞት ማዳን መቻሉን የጠቆሙት ኃላፊው፤ ሁሉም እናቶች በየሶስት እና በየስድስት ወራቱ ምርመራ በማድረግ የራሳቸውን እና የቤተሰባቸውን ጤና መጠበቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎችም የወባን ወረርሽኝ ለመከላከል በአካባቢያቸው ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን ከማፋሰስ ጀምሮ ሌሎችንም ርምጃዎች በመውሰድ የበኩላቸውን ኃላፊነት እየተወጡ መሆናቸውን ገልፀዋል።
በባለሙያዎች በተፈጠረላቸው ግንዘቤ መሰረት የበሽታ ቅድመ ምርመራ በማድረግ የራሳቸውን ጤና ለመጠበቅ በሚደረጉ ጥረቶች ሚናቸውን እንደሚወጡም ገልጸዋል።
ዘጋቢ: ሙዘይን ሰኒ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
በፍትሕ ዘርፍ የሚታየው የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሠራር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ረዳት የመንግሥት ተጠሪ አቶ ደሳለኝ ፈቀደ አስታወቁ
በመስኖ አምርተው የተሻለ ገቢ እያገኙ መሆናቸውን አርሶ አደሮች ተናገሩ
የካፈቾ ዘመን መለወጫ በዓል “ማሽቃሮ” አብሮነትንና ወንድማማችነትን የሚያጎላ ነው – የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ