የሳውላ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

የሳውላ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

በደቡብ ክልል በጎፋ ዞን ለሚገነባው የሳውላ አዳሪ ትምህርት ቤት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።

የመሠረት ድንጋዩን ያስቀመጡት የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌና ሌሎች የፌዴራልና የደቡብ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ስለመሆናቸው የኢዜአ መረጃ ያመለክታል።

ትምህርት ቤቱ በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ያስችላሉ ተብለው ከተያዙ 50 አዳሪ ትምህርት ቤቶች አካል ሲሆን፣ ከትምህርት ቤቶቹ መካከል 5ቱ በደቡብ ክልል እንደሚገነቡ ታውቋል።

ትምህርት ቤቱ በአንድ ዓመት ውስጥ ግንባታው ተጠናቆ በ2017 ዓ.ም የመማር ማስተማር ስራ ይጀመርበታል ተብሏል።

የትምህርት ቤቱን ግንባታ ወጪ ሰዎች ለሰዎች የተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት እንደሚሸፍን ተገልጿል።