በ2015 የተመዘገቡ መልካም ተሞክሮዎችን በማጠናከርና ጉድለቶችን በማረም በቀጣይ በተሻለ ለመፈፀም ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

በ2015 የተመዘገቡ መልካም ተሞክሮዎችን በማጠናከርና ጉድለቶችን በማረም በቀጣይ በተሻለ ለመፈፀም ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

ሀዋሳ፡ ሐምሌ 22/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በ2015 የተመዘገቡ መልካም ተሞክሮዎችን በማጠናከርና ጉድለቶችን በማረም በቀጣይ የተሻለ ለመፈፀም ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት የአስፈፃሚ ተቋማት የ2015 ዕቅድ አፈፃፀምና የ2016 ጠቋሚ ዕቅድ በሚዛን አማን ከተማ ገምግሟል።

በዞኑ የአስፈፃሚ ተቋማት የ2015 ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2016 ጠቋሚ ዕቅድ በሁሉም ዘርፍ ቀርቦ መገመገሙ እና በየዘርፉ የተሻለ አፈፃፀም መመዘገቡ እና ከተደራሽነት ጋር ተያይዘው በትኩረት እንደሚሠራ የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ ቀበሌ መንገሻ ተናግረዋል።

በግብርና ዘርፍ በአትክልት በፍራፍሬና በመሳሰሉት እንዲሁም በሌማት ትሩፋት በእንሰሳት ዝሪያ ማሻሻያ አቅርቦት ላይ የግብኣት ዕጥረት መታየቱ በቀጣይ የሚፈታበት ሥራ ለማከናወን አቅጣጫ ተቀምጧል።

በጤናና ትምህርት ሥራ በጥራት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሠራ እንደሚገባ የገለፁት ዋና አስተዳደሪው የ2015 አፈፃፀም ውጤታማ እና ለተሞክሮ የሚሆኑ አካባቢዎች የታየበት እንደሆነም ተናገረዋል።

እንደሀገር ትኩረት የተሰጠው የወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር ተያይዞ ለወጣቶች የልማት ቦታዎች በመስጠት በኩል የሚታዩ ችግሮች ሊፈቱ እንደሚገባም ዋና አስተዳደሪው ገልፀዋል።

በ2015 የገቢ አፈፃፀም ከዕቅድ በላይ የተከናወነ ቢሆንም ከከተማው የገቢ ምንጭ አኳያ ትኩረት ተሰጥቶ ገቢ የማሰባሰብ ተግባር ሊከናወን እንደሚገባ አፅንኦት ተሰጥቷል።

ህብረተሰቡ የሚጠይቃቸውን ልማቶች በማቅርብ በኩል ገቢ ከፍተኛ ሚና መሆኑና በ2015 በ38 በመቶ ወጪን በገቢ መተካት የተቻለ ሲሆን በ2016 ከ45 በመቶ በላይ እንደሚሠራ መታቀዱን አቶ ቀበሌ አብራርተዋል።

በደቡብ ቤንች ወረዳ የመንገድ፣ የድልድይ እና የምንጭ ግንባታዎች በህብረተሰብ ተሳትፎ በመከናወኑ ተሞክሮው ወደ ሌሎች አካባቢዎች ማስተላለፉ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል።

በ2015 የተከናወኑ ተግባራትን በማጠናከር ጉደለቶችን በ2016 በማሻሻል የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አቶ ቀበሌ አብራርተዋል።

የዞኑ ግብርና አካባቢ ጥበቃ ህብረት ሥራ መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ጉብላ በበኩላቸው በሁሉም ዘረፎች አመረቂ ውጤት መመዘገቡን አውስተው ከማሳ ዝግጅት እስከ ምርት አሰባሰብ በተደረገው ድጋፍ በቆሎ በሄክታር 120 ኩንታል መገኘቱን ገልፀዋል።

ከ5 ሄክታር መሬት በላይ በባህር ዛፍ የተሸፈነው በማስወገድ ከ 5ሺህ በላይ የሙዝ ችግኞችን መትከል መቻሉ በቀጣይ በምስራቅ አፍሪካና በአረብ ሀገራት የሙዝ ምርት ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን ኃላፊው አውስተው በቀን ከ30 እስከ 40 መኪና ምርቱ ለግብይት እየወጣ መሆኑንም ተናግረዋል።

በ2015 የትምህርት ሴክተር በተማሪዎች ውጤት ማሻሻል በ8ኛ ክፍል ክልላዊ እና 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ተፈታኝ ለይ ከመምህራን ጀምሮ የአቅም ግንባታ እንዲሁም የተማሪ መፅሐፍት አቅርቦትና የመሳሰሉት ተግባራት ሲከናወን መቆየቱን አቶ ግዛው ሀይሌ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ገልፀዋል።

የት/ቤቶችን ደረጃ በማሻሻልና ለመማር ማስተማር ምቹ በማደረግ ረገድ “ትምህርት ለትውልድ” በሚል መሪቃል ከ25 ሚሊየን ብር በላይ በጀት በመመደብ እየተሰራ መሆኑን ኃላፊው ጠቅሰው በ2016 የመፅሐፍት አቅርቦት ችግር በመቅርፍ በ2015 በጥንካሬና በጉድለት የታየውን በመውሰድ ለትምህርት ሴክተር መሳካት የሁሉም ኃላፊነት ነው ብለዋል።

አቶ አገኘው ወርቁ የትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ የግብርና የትምህርት፣ የጤና እንዲሁም የፀጥታ ሥራዎችን ለመከወን የመሠረተ ልማት ግንባታ ወሳኝ በመሆኑ የመንገድና የድልድይ ተግባራት በ2015 በተሻለ ሁኔታ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል።

በዚህም በ2015 210 ኪ.ሜ መንገድን በ23 ሚሊየን ብር ለማከናወን ታቅዶ 310 ኪ.ሜ በ35 ሚሊየን ብር መሰራቱን ኃላፊው ገልፀው የትራፊክ አደጋ ለመቀነሰ የፍጥነት መቆጣጠሪያዎችን በመስራት የተሻለ አፈፃፀም መመዘገቡን አብራርተዋል።

በአፈፃፀም ግምገማው በከተማ ልማት በኢንተርፕራይዝ ዘርፍ የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ በንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታና ተደራሽነት የተቋራጡ 7 ፕሮጀክቶች መጠናቀቅ፣ ከኑሮ ውድነትና የገቢ አሰባሰብ የመሳሰሉት ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥተው ተጠናቋል።

ዘጋቢ፡ አብዲሳ ዮናስ – ከሚዛን ጣቢያችን