ባህልና ስፖርትን ለማልማት፣ ለመጠበቅና ለማስተዋወቅ ማህበራዊ መሠረት መያዝ እንዳለበት ተገለጸ

ባህልና ስፖርትን ለማልማት፣ ለመጠበቅና ለማስተዋወቅ ማህበራዊ መሠረት መያዝ እንዳለበት ተገለጸ

‎የኮሬ ዞን ባህልና ስፖርት ጽህፈት ቤት የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 ዓመት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
‎‎
‎የውይይቱን መድረክ በንግግር የከፈቱት የኮሬ ዞን አስተዳዳሪ ተወካይ እና የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አገኘሁ በቀለ ባህልና ስፖርት በየዘርፉ ማሳደግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት እንደሆነ አስረድተዋል።

‎በአሁኑ ወቅት እየታየ ያለውን የስፖርት እንቅስቃሴ አጠናክረን እንቀጥላለን ያሉት አቶ አገኘሁ ባህል፣ ታሪክና፣ ቅርስና ቋንቋ በማልማት ባህል እንዳይበረዝ መታደግ ይኖርብናልም ብለዋል።

‎የኮሬ ዞን ባህልና ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ንጋቱ መሸሻ በዞኑ በርካታ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ቅርሶች መኖሩን አስታውሰው በቀጣይ የማልማት፣ የመጠበቅና የማስተዋወቅ ተግባር እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።

‎የኬሌ ከተማ አስተዳደር አቶ ተማሙ ጀማል በመድረኩ ተገኝተው በአስተላለፉት መልዕክት ባህልና ስፖርት ዘርፍ ማሳደግ አከባቢውን ለማስተዋወቅ፣ ንቁና ብቁ ትውልድን ለመፍጠር የጎላ ድርሻ አለው ብለዋል።

‎የዞኑ ባህል እና ስፖርት ጽህፈት ቤት የስፖርት ውድድር እና የህብረተሰብ ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ አቶ ተበጀ ተፈራ የ2018 ዓመተ ምህረት ተግባር አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ሰነድ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።

‎ከተሳታፊዎች አቶ በሀይሉ በልጂግ፣ ወ/ሮ አስቴር ምልክያስ ባህል ስፖርት ማህበራዊ መሠረት ካልያዘ ማልማት እንደማይቻል በመግለጽ በተለይም ባህልና ስፖርት ከሥር ለመገንባት ከትምህርት በቶች ጋር መሥራት እንደ ሚጠበቅ ተጠቁመዋል።

‎ዘጋቢ፡ ምርጫ መላኩ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን