የደሬቴድ ዲጂታል ሚዲያ የሐምሌ 21/2015 ዓ.ም የዕለቱ ዋና ዋና ዜናዎች፡-
👉በ2015/16 የምርት ዘመን ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ ከታቀደው 15 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል ማዳበሪያ ውስጥ 10 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች መሠራጨቱን የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ አስታወቁ።
👉የአሠራር ማሻሻያዎች፣ የአሠራር ቁጥጥር የተደረገባቸው እና ክፍተታቸው ታይቶ የተደገፉ የልማት ድርጅቶች ወደ ትርፍ መመለስ መጀመራቸውን የመንግሥት የልማት ድርጅቶችና ይዞታ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
👉በደቡብ ክልል እየተተገበረ ያለው የፍራፍሬ ልማት ፕሮጀክት በኑሯችን ላይ ተጨባጭ ለውጥ አምጥቶልናል ሲሉ በጉራጌ ዞን የመስቃን ወረዳ አርሶ አደሮች ገለጹ።
👉በአውቶሞቲቭ ኢንቨስትመንት ዘርፍ እንደ ቮልስዋገን ያሉ አለም አቀፍ አምራቾች እንዲሳተፉና እንዲያለሙ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገለፀ።
👉ተገልጋይን በሚያንገላቱ የመንግስት ሰራተኞች ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል የሲዳማ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡
👉በተያዘው በጀት ዓመት 529 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለጸ።
👉በደቡብ ኦሞ ዞን የቱርሚ ወይጦ 120 ኪሎ ሜትር የኮንክሪት አስፋልት ግንባታ ሥራ ያለበት ችግር ተፈትቶ በተያዘለት ጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ ተጠየቀ።

More Stories
ውድና ውስን የሆነውን መሬት ያለብክነት ለመምራትና ለመጠቀም እየተሰራ ነው – የባስኬቶ ዞን አስተዳደር
በጎፋ ዞን ጋልማ ከተማ በ2019 በጀት ዓመት ከ18 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር መታቀዱ ተገለፀ
የሀድያ ብሔር የዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓልን ለማክበር በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ