የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊና የየዞን ከፍተኛ አመራሮች በሣውላ ማረሚያ ተቋም አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገ/መስቀል ጫላና የ2018 ዓ.ም የአፈፃፀም ግምገማ ለማድረግ ወደ ሳውላ ከተማ ባቀኑበት በሣውላ ማረሚያ ተቋም ተገኝተው የአረንጓዴ አሻራ በማኖር በተቋሙ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ወቅት የግምገማው ተሳታፊዎች ችግኝ በመትከል ለአረንጓዴ አሻራ አስተዋፅዖ አድርገዋል። በተቋሙ የሚከናወኑ የዕደ ጥበብና የሌማት ትሩፋት ሥራዎችንም በመመልከት የሥራዎቹን አፈፃፀም ተመልክተዋል።
የሣውላ ማረሚያ ተቋም ከማረምና ማነፅ ተግባሩ ባሻገር ታራሚዎች የሥራ ክህሎትና የሙያ ብቃት እንዲያዳብሩ የሚያስችሉ የልማት ተግባራትን እያከናወነ መሆኑ በጉብኝቱ ተገልጿል።
በተለይም የዕደ ጥበብ ሥራዎችና የሌማት ትሩፋት ተግባራት ታራሚዎች በሥራ እንዲሳተፉ፣ የተለያዩ ክህሎቶችን እንዲያዳብሩና ወደ ማህበረሰቡ ሲመለሱ በኢኮኖሚ ራሳቸውን ችለው እንዲኖሩ የሚያግዙ መሆናቸው ተጠቁሟል።
አቶ ገ/መስቀል ጫላ ተቋሙ የማረምና ማነፅ ሥራውን ከልማትና ከክህሎት ማበልፀጊያ ተግባራት ጋር በማጣመር ታራሚዎች ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ እና በራሳቸው አቅም መተዳደር የሚችሉ ዜጎች ሆነው እንዲወጡ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የ2018 ዓ.ም. የአፈፃፀም ግምገማ ተሳታፊዎች በሣውላ ከተማ በማረሚያ ተቋሙ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ከመጎብኘታቸው ባሻገር በአረንጓዴ አሻራ ተግባር በመሳተፍ አሻራቸውን አሳርፈዋል።
ዘጋቢ: አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።
የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት ይሠራል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)
ጥራቱ የተጠበቀ ከ500 ቶን በላይ እሸት ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ