በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ እና ልየታ ተካሄደ
የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር በዓለምአቀፍ ደረጃ ከጡት ካንሰር ቀጥሎ ገዳይ በሽታ በመሆኑ ነው በወረዳው ለሚገኙ ሴቶች የምርመራ ዘመቻው የተካሄደው።
በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተካልኝ ጥላሁን ከጤና ተቋም ራቅ ያሉ ሴቶች ህክምና እንዲያገኙ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የምርመራ እና የልየታ ዘመቻ እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በወረዳው ባሉ ሁሉም ቀበሌያት የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር፣ ሲኖግራፊ፣ የደም ግፊት እና የስኳር በሽታዎችን በዘመቻ መልክ በምርመራ የመለየት ሥራ እየሠሩ መሆናቸውንም ኃላፊው አስረድተዋል።
ግራውንድስ ፎር ሄልዝ አስተባባሪ አቶ መስፍን ዋና በበኩላቸው፣ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር በዓለም አቀፍ ደረጃ ከጡት ካንሰር ቀጥሎ ገዳይና አደገኛ በሽታ በመሆኑ ሴቶች በንቃት ተመርምረው ራሳቸውን ማወቅ እንዳለባቸው ገልጸዋል።
የአንዲት ሴት ሕይወት ዋጋ ስላላት በማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ላይ ትኩረት አድርገው እየሠሩ መሆናቸውን በመግለጽ ከልየታ በኋላ በጊዜ ህክምና የሚያገኙበት ሁኔታ መመቻቸቱን አስተባባሪው ጠቁመዋል።
በወረዳው የቆንጋ ጤና ጣቢያ እና የብርብስ ቄላ ጤና ኬላ ባለሙያዎች ወይዘሮ አበበች ባፋ እና መሠረት ታደሰ እንደተናገሩት፤ የምርመራው ሂደት ቀድሞ ከነበረው የተለየ በመሆኑ በቀላሉ መጨረስ እንደሚቻል ነው የገለጹት።
በማህበረሰቡ የግንዛቤ ዕጥረት በመኖሩ ወደ ጤና ጣቢያ በመሄድ እንዲመረመሩ የቅስቀሳ ሥራ እያከናወኑ መቆየታቸውን ያነሱት ባለሙያዎቹ በዚህም በርካታ ሴቶች ተጠቃሚ መሆናቸውን አስረድተዋል።
ምርመራ ሲያደርጉ አግኝንተን ያነጋገርናቸው ወይዘሮ ፀሐይነሽ እሸቱ፣ ዘለቀች ባርሳ እና ሌሎችም የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ አካባቢያቸው ላይ በመምጣቱ መደሰታቸውን በመግለጽ ምርመራው ራስን በማወቅ ቶሎ ህክምና ለማግኘት እንደሚረዳቸውም ተናግረዋል።
ዘጋቢ: አሀዱ አሸናፊ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ እና ልየታ ተካሄደ

More Stories
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።
የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት ይሠራል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)
ጥራቱ የተጠበቀ ከ500 ቶን በላይ እሸት ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ