ማንቸስተር ሲቲ ኤሊዮት አንደርሰንን በይፋ አስፈረመ
የእንግሊዙ ክለብ ማንቸስተር ሲቲ ኤሊዮት አንደርሰንን ከኖቲንግሃም ፎረስት የክለቡ ክብረወሰን በሆነ የዝውውር ሒሳብ በይፋ አስፈርሟል።
ማንቸስተር ሲቲ ለእንግሊዛዊው አማካይ 116 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሒሳብ መክፈሉ ተገልጿል።
የ23 ዓመቱ አንደርሰን ከማንቸስተር ሲቲ ጋር የአምስት ዓመታት ኮንትራት ተፈራርሟል።
ዝውውሩን በአሜሪካ ሆኖ ያጠናቀቀው ኤሊዮት አንደርሰን በማንቸስተር ሲቲ ቤት በሳምንት 300 ሺህ ፓውንድ ክፍያ እንደሚያገኝ ተዘግቧል።
ዝውውሩ ተጫዋቹን የምንግዜም ውዱ ፈራሚ ብሪታንያዊ ተጫዋች አድርጎታል።
አንደርሰን በአዲሱ አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ስር የመጀመሪያው ፈራሚ ሆኗል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ኤርሊንግ ሀላንድን አምበል የምናደርገዉ ከሆነ ትልቅ ችግር ዉስጥ እንገባለን” ኤንዞ ማሬስካ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ጆርጂና ሮድሪጌዝ የጋብቻ ስነ ስርዓታቸውን ፈፀሙ
ሶማሊያዊው ዳኛ ኦማር አርታን የዩኤፋ ሱፐር ካፕን በዋና ዳኝነት በመምራት የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሊሆኑ ነው