ቼልሲ ማርኮ ፓሌስትራን አስፈረመ
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ማርኮ ፓሌስትራን ከአትላንታ ማስፈረሙን በይፋ አስታውቋል።
ቼልሲ ጣሊያናዊውን የቀኝ መስመር ተከላካይ ለማስፈረም 47 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ አድርጓል።
የ21 ዓመቱ ማርኮ ፓሌስትራ በሰማያዊዮቹ ቤት እ.ኤ.አ እስከ 2032 ድረስ የሚያቆየውን የ6 ዓመት ኮንትራት መፈረሙ ተገልጿል።
ማርኮ ፓሌስትራ በአሰልጣኝ ዣቪ አሎንሶ የቼልሲ አሰልጣኝነት ዘመን የመጀመሪያው ፈራሚ ሆኗል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
ቼልሲ ማርኮ ፓሌስትራን አስፈረመ

More Stories
ከጠጠር ሜዳ እስከ ፕሪሚየር ሊግ
ሞሮኮ እና ብራዚል ወደ ቀጣዩ ዙር ሲያልፉ ጀርመን ተሰናበተች
የአንደኛ ደረጃ አትሌትክስ አሰልጣኞች ተመረቁ