ለደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እና ለቅርንጫፍ ጣቢያ አመራሮችና ጋዜጠኞች የአሠልጣኞች ስልጠና እየተሰጠ ነው
ሀዋሳ ፡ ሰኔ 22/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የብዝሃነት ድምፅ የሆነው ደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ለማዕከልና ቅርንጫፍ ጣቢያዎች አመራሮችና ጋዜጠኞች በ”ሕብረ -ብሔራዊ የፌደራል ሥርዓት” ዙሪያ የአሠልጣኞች ስልጠና በሀዋሳ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል።
በስልጠና መድረክ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ሬ/ቴ/ድ/ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘላለም ገነሞ እንደገለጹት፥ የህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ጋዜጠኞች በዕውቀት ላይ በተመሠረተ መልኩ መረጃ ለህዝቡ እንዲያደርሱ የራሱ የሆነ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
ማዕከሉ ለደ/ሬ/ቴ/ድ ዘርፈ ብዙ እገዛ እያደረገ እንደሚገኝ እና በቀጣይም ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
ከደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ጋር በቀጣይ የህገ መንግስትና የፌደራሊዝም አስተምህሮና የሚዲያ ፎረም በማቋቋም እንዲሁም በብዝሃ ቋንቋዎች አስተምህሮ እስከአሁን እየተሰራ ካለው በላቀ ደረጃ ይሠራል ያሉት ደግሞ የህገ መንግስትና የፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኃይለየሱስ ታዬ ናቸው።
በስልጠና መድረክ” የሕብረ ብሔራዊ ፌዴራሊዝም ስርዓት ጽንሰ ሀሳብ እና የተመረጡ ተሞክሮዎች” የሚል ሠነድ በዋና ዳይሬክተሩ ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
ዘጋቢ ፡ ታሪኳ በቀለ

More Stories
የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት የትምህርት ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ግምገማ እና የ2019 ዓ.ም የተማሪዎች ቅበላ የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው
የዳውሮ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ ሥራ ዘመን 29ኛ መደበኛ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ
የህግ ታራሚዎችን አምራች ዜጋ ለማድረግ የስነ-ልቦና ድጋፍና የክህሎት ማጎልበቻ ስራዎች ወሳኝ መሆናቸው ተገለጸ